From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
"ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
የእግዚአብሔርን ፡ ጦርነት ፡ ስንዋጋ
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው"
አዝ፦ ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
የእግዚአብሔርን ፡ ጦርነት ፡ ስንዋጋ
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
ያየነውን ፡ ኢላማውን ፡ አንስትም
የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ እናፈርሳለን
የእግዚአብሔር ፡ ወታደሮቹ ፡ ነን
እንተጋለን ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ አንልም (፪x)
አዝ፦ ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
የእግዚአብሔርን ፡ ጦርነት ፡ ስንዋጋ
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
ወገባችሁን ፡ በእውነት ፡ ታጥቃችሁ
የጽድቅንም ፡ ጥሉን ፡ ለብሱቹህ
በሰላም ፡ ወንጌል ፡ በመዘጋጀት
እግሮቻቹህ ፡ ተጫመው ፡ ይቁሙ (፪x)
አዝ፦ ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
የእግዚአብሔርን ፡ ጦርነት ፡ ስንዋጋ
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
የእግዚአብሔርን ፡ ጦርነት ፡ ስንዋጋ
ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፬x)
|