እንጸልይ (Entseley) - ፌበን ፡ ደምሴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌበን ፡ ደምሴ
(Feben Demissie)

Feben Demissie 1.jpg


(1)

ይሳካል
(Yesakal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌበን ፡ ደምሴ ፡ አልበሞች
(Albums by Feben Demissie)

 
ጊዜው ፡ እየከፋ ፡ ሲሄድ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርጋል
ጥፋት ፡ ሲበዛ ፡ ወዴት ፡ ይሸሻል
መተማመን ፡ ጠፍቶ ፡ ጥላቻ ፡ ሲበረታ
የተለፋበት ፡ ሁሉ ፡ ድርምስምስ ፡ ሲል
ቀና ፡ ነው ፡ የተባለው ፡ ቅጡ ፡ ሲጠፋ
ሰው ፡ ግራ ፡ ተጋብቶ ፡ ጭንግር???ጭምር??? ፡ ሲለው
ወደማን ፡ ነው ፡ የሚያየው

አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ
እንጸልይ ፡ ሳንታክት
እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ
አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x)

በድህነት ፡ ቀመር ፡ ተጠፍሮ
ህዝብ ፡ በድካም ፡ ጅራፍ ፡ ሲገረፍ
ሞትን ፡ እንደጨለማ ፡ ምድራችንን ፡ ሲከብ
አንዱ ፡ ከአንዱ ፡ ሲጋደል
አለቆች ፡ አልፈቱም ፡ ይህን ፡ እንቆቅልሽ
ከአዋቂቆችም ፡ ምክር ፡ አልተገኘም
ነገሥታት ፡ እነርሱ ፡ ተሰወረባቸው
ድንግዝግዝ ፡ አለ ፡ ቀኑ

አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ
እንጸልይ ፡ ሳንታክት
እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ
አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x)

እንጸልይ

በስሜ ፡ የተጠሩ ፡ ህዝቤ
ራሳቸውን ፡ አዋርደው ፡ ቢጸልዩ
ከሰማይ ፡ ሆኜ ፡ እሰማለሁ
ምድራቸውን ፡ እፈውሳለሁ
ብሏል ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ
እንጸልይ ፡ ሳንታክት
እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ
አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x)

እንጸልይ