በሙሉ ፡ ልባችን ፡ እናመልክሃለን (Bemulu Lebachen Enamelkehalen) - ፌበን ፡ ደምሴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፌበን ፡ ደምሴ
(Feben Demissie)

Feben Demissie 1.jpg


(1)

ይሳካል
(Yesakal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፌበን ፡ ደምሴ ፡ አልበሞች
(Albums by Feben Demissie)

 
እግዚአብሔር ፡ ምናመልክህ ፡ አስከብረኀን ፡ አይደለም
ብናመልክህ ፡ ብንሰግድልህ ፡ ስለተገባህ
የምትወደድ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ላወቀህ ፡ ለቀረበህ
ፍቅርህ ፡ ያዘምረናል ፡ ምሥጋናህ
እናመልክሃለን ፡ እግዚአብሔር

አዝ፦ በሙሉ ፡ ሃይላችን ፡ በሙሉ ፡ ነፍሳችን
በሙሉ ፡ ልባችን ፡ እናመልክሃለን (፪x)

የዘለዓለማዊው ፡ መንግሥት ፡ አምባሳደሮች ፡ ልንሆን
ልትወደን ፡ ልትመርጠን ፡ አላፈርክብን
ልጆቼ ፡ ብለህ ፡ ጠራኀን ፡ አባ ፡ አባት ፡ ልንልህ ፡ ፈቀድክ
በድፍረት ፡ ፊትህን ፡ ልናይ ፡ ብቁ ፡ አደረግከን
እናመልክሃለን ፡ እግዚአብሔር

አዝ፦ በሙሉ ፡ ሃይላችን ፡ በሙሉ ፡ ነፍሳችን
በሙሉ ፡ ልባችን ፡ እናመልክሃለን (፪x)

አባትነትህን ፡ ለማግኘት ፡ ከእኛ ፡ ምንም ፡ አላስከፈልክ
ይልቁን ፡ ልጅህን ፡ ሰጥተህ ፡ ከእኛ ፡ ታረቅህ
እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አንተ ፡ ለእኛ ፡ ያሳየኀው
ለአንተ ፡ መኖር ፡ መስገድ ፡ መቀኘት ፡ ሲያንስህ ፡ ነው

አዝ፦ በሙሉ ፡ ሃይላችን ፡ በሙሉ ፡ ነፍሳችን
በሙሉ ፡ ልባችን ፡ እናመልክሃለን (፫x)

በሙሉ ፡ ልባችን ፡ እናመልክሃለን (፭x)