በብዛት ፡ የሚጠየቁ ፡ ጥያቄዎች (Frequently Asked Questions)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በዚህ ፡ ገጽ ፡ ላይ ፡ እንዲካተት ፡ የሚፈልጉት ፡ ጥያቄዎች ፡ ካሉ ፡ እዚህ ፡ ይጫኑ

1) ለምን ፡ ሙዚቃ ፡ ከመዝሙሮች ፡ ጋር ፡ አታወጡም?

መዝሙሮችን ፡ ያለ ፡ ዘማሪያን ፡ ወይም ፡ አከፋፋዮች ፡ ፈቃድ ፡ አናወጣም ። እንዲሁም ፡ "ያለፈቃድ ፡ አውጥተን ፡ ከተቃወሙን ፡ እናወርደዋለን" ፡ የሚል ፡ አመለከከት ፡ የለንም ። ያለፈቃድ ፡ ማውጣት ፡ በአብዛኛው ፡ አገሮች ፡ ሕገወጥ ፡ ነው ። የምናወጣው ፡ አስቀድመን ፡ ፈቃድ ፡ ካገኘን ፡ ብቻ ፡ ወይም ፡ ዘማሪያኖች ፡ ራሳቸው ፡ መዝሙሩን ፡ በነጻ ፡ ከለቀቁት ፡ ብቻ ፡ ነው ።

2) የእምነታችሁን ፡ ገለጻ ፡ የት ፡ ነው ፡ የማነበው?

የእምነታችን ፡ መግለጫ ፡ በዚህ ፡ ገጽ ፡ ጋር ፡ ይገኛል ።

3) መዝሙር ፡ መግዛት ፡ እፈልጋለሁ ፡ ልትሸጡልኝ ፡ ትችላላችሁ?

በዚህ ፡ ጊዜ ፡ እኛ ፡ የምንሸጠው ፡ ሙዚቃዎች ፡ የሉም ። ነገር ፡ ግን ፡ ሌሎች ፡ ወደሚሸጡበት ፡ ድረ ፡ ገጾች ፡ እንልኮታለን ፡ በተቻለን ፡ መጠን ።

4) እንዴት ፡ መዝሙር ፡ ግጥም ፡ ልልክላቹህ ፡ እችላለሁ?

መዝሙር ፡ ግጥም ፡ በዚህ ፡ ገጽ ፡ ሊልኩልን ፡ ይችላሉ ። ካልተመቾት ፡ በኢሜይል ፡ መላክ ፡ ይችላሉ ።

5) በስልክ ፡ ለመጠቀም ፡ የሚረዳ ፡ አፕ (App) ፡ አላችሁ ፡ ወይ?

በዚህ ፡ ሰዓት ፡ ለአንድሮይድ ፡ የሚሆን ፡ አፕ ፡ አለን ። ይህ ፡ ለማግኘት ፡ እዚህ ፡ ይጫኑ ። ለአፕል ፡ የሚሆን ፡ አፕ ፡ እየተሰራ ፡ መሆኑን ፡ መግለጽ ፡ እንፈልጋለን ።