ዛሬም አለሁ (Zarem Alehu) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

አብዝቼ ጨምሬ ስምህን ልባርከው
ኢየሱስ አንተ ነህ ነፍሴን የወደድከው
አብዝቼ በብዙ ስምህን ልባርከው
ኢየሱስ አንተ ነህ ነፍሴን የወደድከው

እስኪ ጨማምሬ ስምህን ልባርከው
ያደረክልኝን ምህረት እያየሁ
እስኪ ጨማምሬ ስምህን ላክብረው
የሰራህልኝን በጎነት እያየሁ

እየወደድከኝ ዛሬም አለሁ
እየራራህልኝ ዛሬም አለሁ
ይቅር እያልከኝ ዛሬም አለሁ
ሕይወት ሆነኸኝ ዛሬም አለሁ

እንደገና/3 በፍቅርህ አቀረብከኝ
እንደገና ልጅህ አደረከኝ
እንደገና/3 በምሕረትህ አዘንክልኝ
እንደገና የአንተ አደረከኝ

ያወቅሁት እውነት የተረዳሁት
ምሕረትህ ገኖ እንዳለሁ በሕይወት
የሚገባኝ ይሄ ነው በየዕለት

ፍቅርህ አልራጠም ምሕረትህ አልነጠፈም
የትላንት መውደድህ ለብ እንኳን አላለም

እየወደድከኝ ዛሬም አለሁ
እየረዳኸኝ ዛሬም አለሁ
እያፅናናኸኝ ዛሬም አለሁ
እያፀናኸኝ ዛሬም አለሁ

ክብር ይሁን ለዘለዓለም
ምስጋናን ለአንተ ለዘለዓለም
ቸር አምላክ ነህና ለዘለዓለም
የሚመስልህ የለም ለዘለዓለም

ለዘለዓለም እንዳንተ ያለ የለም
ለዘለዓለም የሚመስልህ የለም