ይችላል (Yichelal) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

እናንተ ደካሞች ብዙ ሸክም የከበዳችሁ
ወደ እኔ ቅረቡ ከቀንበራችሁ ላሳርፋችሁ
ብሏል እና ጌታ ሸክሜን ሁሉ አንድም ሳላስቀር
አራግፋለሁ ጭንቀቴን ሁሉ ከእግሩ ስር

እኔን ያጎበጠኝ በእርሱ ፊት ምንድነው
አልፈታ የሚለው ችግር የትኛው ነው
ጥያቄዬን ሁሉ ሰዳለሁ ወደላይ
ለእርሱ አስረክቤ እኔ እላለሁ እፎይ

ይችላል/4
ይችላል ሽባውን መተርተር
ይችላል ድዳውን ማናገር
ይችላል ተራራውን መናድ
ይችላል ደመናውን ማውረድ

አለቀልኝ ብዬ ያከተመው ነገሬን ይዤ
ስለምን ልቀመጥ አንተ እያለህ በሀዘን ተክዤ
ትላንትን ስትሰራ ስታደርግ በአይኔ አይቼ
ስለምን ልጠርጥር ዛሬ የተራራውን ትልቀት ፈርቼ

ተራራው ለእኔ እንጂ በአንተ ፊት ምንድነው
የሚገዳደርህ ሀይል የትኛው ነው
አንዳች ነገር የለም ከአንተ አቅም በላይ
ሁሉን የምትችል ጌታ አይደለህም ወይ

ይችላል/4
ይችላል እንቆቅልሽ መፍታት
ይችላል ያዘነን ማፅናናት
ይችላል የወደቀን ማንሳት
ይችላል ጨለማውን ማብራት

ከከበበኝ በላይ ያንተ ትልቅነት ይታየኛል
ያንተ ትልቅነት ይከብድብኛል
አምንሀልሁ ጌታ ሁሉ ይቻልሀል
ምን ተስኖህ ሁሉ ይቻልሀል ምን ያቅትሀል

ትሰራለህ ታደርጋለህ የሚሳንህ የለም
ትተክላለህ ትነቅላለህ ከልካይ የለብህም
ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሆ ሁሉን ትችላለህ
ኤልሻዳይ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ

ትችላለህ የጠፋን መመለስ
ትችላለህ በሽታን መፈወስ
ትችላለህ ሸለቆን መሙላት
ትችላለህ የሞተን ማስነሳት