የበረሀው ጓዴ (Yeberehaw Guade) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ማን ነበረ ከጎኔ ያኔ
ያልተለየኝ ከአጠገቤ
ሀዘን ሲያቆስለው ልቤን
ሳስታውሰው መከራዬን
የተወለድኩበትን ቀን ስረግመው ደጋግሜ
አንዱ ሳያበቃ የኑሮዬ ሲቃ
ሲደራረብብኝ ውስጤን ሲደቁሰኝ
በእውነት ነበረኝ ወይ እውነተኛ አፅናኝ
የውስጥ ጥልቅ ስሜቴን አውቆ የተረዳኝ
ፈራጅ እንጂ አፅናኝ ነበረኝ ወይ
የመሰለውን የተሰማውን ባይ
አዝነው ሲያስተክዙኝ መልሰው ሲያቆስሉኝ
ብሶቴን ቀስቅሰው አልቃሻ አደረጉኝ

           የበረሃው ጓዴ የጥሻው ዘመዴ
           ለካስ ወዳጅ አለኝ ባያየው ይህ አይኔ
           ከወንድም አብልጦ በጣም የሚጠጋ
           ተረድቶ የሚረዳ ስለእኔ አለው ዋጋ
                 አለው ባዬ መከታዬ
                ኢየሱስ ጌታዬ
                  ልጄ አትፍሪ ተደገፊ
                  ትከሻዬ ሰፊ
           እያለ ያፅናናኝ ያበረታኝ ክንዴ
           ከጎኔ የቆመ ያባበለኝ ውዴ
           እንባዬን ጠራርጎ አፌን በሳቅ ሞላ
           መከራዬ ሄደ ቀረ ወደኋላ

          <ኢየሱስ> እውነተኛ ወዳጅ
          <ኢየሱስ> ከልብ የሚወዳጅ
          <ኢየሱስ> ታማኝ ባልንጀራ
          <ኢየሱስ> <ቀን ሲጥል የማይከዳ>