ያቺ ጉጠት (Yachi Gutet) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ሳበኝ ወደ አንተ እሮጣለሁ
መልካሙ እረኛ
ድምፅህን (ኮቴህን) እየሰማሁ እከተልሀለሁ

ያቺ ጉጠት ኢሳያስን የዳሰሰች
አንደበቱን ንግግሩን የለወጠች
ዛሬም ትምጣ በነፍስ ስጋ በመንፈሴ
እንዲወገድ ከሕይወቴ ድንዛዜ

ሀይል ያስፈልገኛል የእግዚአብሄር እሳት
ሙሴ በቁጥቋጦ ውስጥ ስትነድድ ያያት
ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በሕይወቴ
አንድ ግዜ ንካኝ ይለወጥ ሕይወቴ

ከአለም መጎምዠት ከስጋዊ መሻት
ውስጡ ወና ባዶ ውሸት እና ቅዠት
ከምናቡ አለም በአምሮት ከመስከር
ህልሜ መና ሆኖ በምኞት እንዳይቀር
ነጥቆ በሚያወጣው ከዘቀጠው ሀሳብ
በምንፈስህ ላምልጥ ከሌለበት እረፍት
ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በሕይወቴ
አንድ ግዜ ንካኝ ይለወጥ ሕይወቴ

የመንፈስህ እሳት የክብርህ ሙላት
ሲያገኘኝ ሲነካኝ ያንተ መገኘት
እንደ ሌላ ሰው እለወጣለሁ
ደጋግመህ ንካኝ መቼ እረካለሁ

ህልውናህ መንፈስህ ነፍሴን ደስ ያሰኛል
ህልውናህ መገኘትህ ነፍሴን ያረካታል
የናፈቀኝ የጠማሁት የምፈልገው የሚናፍቀኝ
ክብርህን ነው ክብርህን
መንፈስህን ነው ክብርህን
ክብርህን ነው ክብርህን
መንፈስህን ነው መንፈስህን