From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ
ከእርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ
ጣዕመ ቢስ ልሳኔን አንደበቴን በራ
ሕይወቴ ጨፍጋጋ እንዳይሆን መራራ
አመዴን አራግፎ ወዛም ያደረገኝ
በሰዎች ሁሉ ፊት በሞገስ አቆመኝ
ደብዛዛው መልኬ ደመቀ በስሙ
ጭንጋፉ ወዜ ተዋበ በደሙ
በድቅድቁ ለሊት በማይሸፈን ፊት
እንዳብለጨልጭ ጌታዬ ልክ እንደመስታወት
የፊቱ ብርሀን ፍንትው ያለ ጮራ
እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ
የፊቱ ብርሀን ወለል ያለ ጮራ
እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ
በራ በራ የሕይወቴ ጭጋግ ወገግ አለ በራ ፈካ /2
በቀን ከሚበረው አስደንጋጭ ፍላፃ
ነፍሴ እርፍ አለች በአንተ ወጥታ ነፃ
የቀትሩ ጋኔል እንዳያስፈራራኝ
መቅሰፍት ወደቤቴ እንዳይገባ ጋረደኝ
መላዕክቱን ሰለ እኔ እያዘዛቸው
እንዳልሰናከል ያዙኝ በእጆቻቸው
የኩላ እና እባቡን እረጋግጬ
ድል አድራጊ ሆንኩ በኢየሱስ
ወጥመዱን አምልጬ
በባላንጣዬ ፊት ራሴን ቀብቶታል
ያስፈራኝ ጠላቴ በተራው ፈርቶኛል
ፀና ፀና የሕይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና /2
ማረፊያዬ ነው የቀትር ጥላዬ
ከእርሱ የተነሳ ፈርቶኛል ጠላቴ
ምን ይዋጠኝ ብዬ ለነገ እንዳልሰጋ
ጽኑ የተስፋ ቃል እኔ አለኝ እርሱ ጋር
በእጄ የያዝኩት ቢወድቅ ቢናድ የካብኩት
ኢየሱስ ስላለኝ አልርበተበትም
በትርህ ምርኩዜ ለሽምግልናዬ
ቀሪ ሀብቴ ነው ቢጎብጥ ጀርባዬ
እስከ ሽበቴ ይሸከመኛል
የማታ የማታ መጦሪያ ኢየሱስ ይሆነኛል
ቸርነት ምሕረቱ ሁሌ ይከተሉኛል
ዘላለም በቤቱ አዝልቆ ይኖረኛል
ፀና ፀና የሕይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና /2
ትሩፋቴ ነው የማታ እንጀራዬ
ከእርሱ የተነሳ ያምራል እርጅናዬ
|