ወዶኛልና (Wedognalena) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ምን ውጦኝ ነበር አንተን ባላገኝ
ባትቀበለኝ ልጅ ባታደርገኝ አሄ
ሰጥተኸኝ ጥበብ ክህሎት ችሎታ
አምላኬን ትቼ ለሰው ሆይ ሆይታ አሄ
ነበር እጣዬ አይኔ ባይበራ
የሲኦል ማገዶ ኑሮ ከሞት ጋር
በራልኝና የሕይወት መንገድ
ኑሮ ጀመርኩኝ ባንተ ስወደድ

ዛሬ ግን ለእየሱስ ዘምራለሁ ዘምራለሁ
ዘምሬ የማልጠግበው ሰለእርሱ ነው
ዛሬ ግን ለክብሩ አወራለሁ አወራለሁ
አውርቼ የማልጠግበው ሰለእርሱ ነው

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
ኧረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስኪ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ከሕይወት ምንጭ ውሀ ፈልቆ ጠጣሁና
ጥሜ ቆረጠልኝ ዳግም ላልጠማ
የክብሩ ነፀብራቅ በላዬ ላይ በርቶ
ከክብር ወደ ክብር አሻገረኝ መርቶ

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
ኧረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስኪ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

የፊቱ ብርሀን አበራ በቤቴ
ጉሙ በነነ ፈካ ሕይወቴ
ተጥለቀለኩኝ በደስታ በሀሴት
ከላይ ወረደልኝ ፍጹም በረከት

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
ኧረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስኪ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው
አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ
ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው
አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ

ከዘለዓለም ማዕድ ከእንጀራው በልቼ
ላልራብ እረካሁ እየሱስን አግኝቼ
የመቅበዝበዝ ሕይወት ከእንግዲህ አበቃ
አይኖቼን ከፈተ ሙት መንፍሴ ነቃ

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
ኧረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስኪ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው
አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ
ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው
አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ