ምትኬ (Mitike) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:49
ጸሐፊ (Writer): ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ቀረብኩ ከችሎት ከፍርድ አደባባይ
ሊገለጥ ሊነገር ታሪኬ እንዲታይ
ብዙ ነው በደሌ ዶሴ ሲወሳ
በነፃ እንድለቀቅ ያሻል የደም ካሳ

በድንገት አንድ ድምጽ ተሰማ ከሰማይ
አገኘዋለው ባይ ስለእኔ ተወካይ
የስራዬ ዋጋ ነበር የሞት ቅጣት
ምትኬ ሆነልኝ በእኔ ፈንታ ሊሞት

በበደል በኃጥያቴ ሙታን የነበርኩኝ
ለዚህ አለም ገዢ የተንበረከኩኝ
የስጋን ምኞቴን ሁሌ የምሰማ
የቁጣ ልጅ ነበርኩ ምኖር በጨለማ

ነገር ግን እግዚአብሄር ምሕረቱ የበዛ
አንድ ልጁን ሰጠኝ እንዲሆነኝ ቤዛ
ክርስቶስን ሳምን ስለው ቤዛ አዳኜ
ተወለድኩ በዚያን ቀን አዲስ ፍጥረት ሆኜ

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም
ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ
በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ

የወደድኳት አለም ያሞካሸኋት
መልሳ ላትበጀኝ ስትነዳኝ ወደ ሞት
እያሳሳቀችኝ አለሁኝ እያለች
ነፍሴን ልታጠፋ በብርቱ ቸኮለች

ሞት እንደሰነቀች ሳይገባኝ ሚስጥሯ
ቀርቤ ሳለሁኝ ለክፉ ወጥመዷ
የአዳኙ ጥሪ ተሰማኝ ከሩቁ
የምሕረት እጆቹ ነፍሴን ተናጠቁ

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም
ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ
በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ

አይወዳደርም የሰጠኝ ፍቅር
በዚህ አለም ክብር
አይነፃፀርም የሰጠኝ ሕይወት
በዚህ አለም ውበት
አይወዳደርም የሰጠኝ ፀጋ
በዚህ አለም ዋጋ
አይነፃፀርም የሰጠኝ ደስታ
በዚህ አለም ሁካታ

በቃ ተለውጫለሁ ልቤን ሰጥቼሀለሁ
ግባ የክብሬ ንጉስ አንተ ሁን የቤቴ ራስ/2

ዕርግማኔን ሁሉ በመስቀል ቸንክሮ
በነጻ ለቀቀኝ ወጥመዴን ሰባብሮ
የሞት ፍርሀት ጫናው ከኔ ላይ ወደቀ
ጠላቴ ላይከሰኝ ነፍሴን አፀደቀ

እኔ የእኔ አይደለሁም ሞቻለሁ ለእራሴ
በቀራንዮ መስቀል በሞቱ አብሬ
በተሻለው ኪዳን በትንሳዔው ጉልበት
ኑሮ ጀምሬያለሁ ሆኜ አዲስ ፍጥረት

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም
ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ
በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ