ለካ ያየኛል (Leka Yayegnal) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ጭው ባለው ምድረበዳ ምንም በሌለበት ውሀ
ባዶ ሆኖ ምንጩ ደርቆ በእጄ የያዝኩት ሁሉ አልቆ
አይኔን ባቀና ወደላይ ስመለክት ወደሰማይ
በተስፋ ተሞላ ልቤ ያየኝን ሳይ አሻቅቤ

ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ

ቃልኪዳኑን የማይረሳ የወደቀን የሚያነሳ
አለን በሰማይ ሊቀ ካህን በድካማችን የሚራራልን
እንዳየ እንደሰማ የማይፈርድ ሀብታም ድሀን እኩል የሚወድ
ፊት አይቶ ፍርድ የማያደላ ለጨነቀው የሚሆን ከለላ

ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ

ጉደለቴን ሳየው ባዶነቴን ይሰብከኛል አወይ ውድቀቴን
እዬዬ እላለሁ እጮሀለሁ የሚረዳ አምላክ እንደሌለው
ሰማይ እና ምድርን የፈጠረ ጌታ አይኔ ተከፍቶ ሳይ አለ በዚህ ቦታ/2

ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ

አቤቱ በስምህ ታመንኩ ለዘላለም
ጥላዬ ነህና ከእንግዲህ አልፈራም
ከማህፀን ጀምሮ የያዙኝ እጆችህ
እግሮቼን አጸኑ እነዚያ ክንዶችህ
ከአመጸኛው ጡንቻ ከአስፈሪው እርግጫ
ነፍሴን አስጥለሀል ከሚወጠኝ ጉድጓድ
ዘመኑን እያየሁ ስለምን ልጨነቅ
አንተን እየጠራሁ አመልጣለሁ ከጭንቅ