እረግረጉ ደረቀ (Eregregu Dereke) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

እግዚአብሄር ከእኔ ጋር ባይሆንማ ኖሮ
የጠላቴ ቁጣ በእኔ ላይ በርትቶ
በሕይወት ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበረ
ታሪኬን ሊያስቀረው ያለ እንዳልነበረ
ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም
እንዳሰበው ክፉ አላገኘኝም
ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም
እንዳሰበው ጠላት አላጠፋኝም

ጠላቴማ ሊለያየኝ ስንት ግዜ ሞከረ
ሊነጥለኝ ከሕይወት ስንት ግዜ ጣረ
ጌታ ጣልቃ እየገባ ምክሩን እያፈረሰ
የሸፈተው ልቤን ወደ እራሱ መለሰ

በጸሎቴ አለፍኩት አልልም ያንን ሁሉ ወጀብ
በጉልበቴስ መች በተንኩት አስፈሪውን አጀብ
በፅናቴ ተወጣሁት አልልም ያን ዳገት አቀበት
በብልጠቴስ መች ሾለኩኝ ከዚያ ሁሉ ወድቀት

ጸጋህ ተትረፍርፎ ምሕረትህ በዝቶልኝ
የማልችለው ተቻለኝ ከባዱ ቀለለኝ
እረግረጉ ደረቀ ጎርባጣውም ቀና
ለዘመመው ማገሬ እንደገና ፀና

ሰባራውን ድልድይ እየገጠመ ጎርፉን እየገደበ
ስፍገመገም እጄን በእጁ ይዞ እኔን አሻገረ
በስሙ አለት ላይ አፀናኝና እንዳወራ የእርሱን ዝና
ዜማን እና ቅኔን አስታጠቀኝ ዘምርለታለሁ ገና
አዜምለታለሁ ገና እቀኝለታለሁ ገና
እኖርለታለሁ ገና አገለግላለሁ ገና