አወራታለሁ (Aweratalehu) - ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

የጸጋውን ቁርበት
(Yetsegawin Qurbet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2021)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ 'ጄሪ' ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነዉ
የሚወደድ ማይጠገብ ለሚጠራው
ነፍሴን ከሞት መለሰ
ፍቅርህ እንደ ጅረት እየፈሰሰ
መንፈሴን አረሰረሰ ህይወቴን እየፈወሰ
መንፈሴን አረሰረሰ ስጋዬን እየፈወሰ

ለስብራቴ ፍቱን መድሐኒቴ
መድመቂያ ካባዬ ለማንነቴ
ስሙ ነው ትምክህቴ መቆሚያ አለቴ
ማገሩ ለቤቴ ፅኑ መሠረቴ

የክብር ንጉሥ ነህ ደጉ ኢየሱስ
ለዘለዓለም ንገሥ
በመንበሬ በኑሮዬ
በሰገነቴ በከፍታዬ
ለዘለዓለም ንገሥ
አንተ የክብር ንጉሥ

ወደዱህ ወደዱህ ያዩ የቀመሱ
ባንተ ደስ አላቸው ሐሴት አደረጉ
መዓዛህ መልካም ነው ስንቱን ለወጠ ስንቱን አጣፈጠ
ፍቅርህ ልዩ ነው ስንቱን ለወጠ ስንቱን አጣፈጠ

የእኔነቴ ማዕረግ የክብር መጠሪያዬ
ኢየሱስ አንተ ነህ ጌጤ መዋቢያዬ
ነፍሴ እንድታውቅህ አንተን እሰብካታለሁ
ልቤም አንዲወድህ ሁሌ አስብሃለሁ

     <አወራታለሁ ለነፍሴ ስላንተ አብዝቼ ሁልጊዜ>
     <እነግረዋለሁ ለልቤ ፍቅርህ እንዲበረታ በሀሳቤ>