Eyerusalem Negiya/Qen Sale/Yeziema Gizie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

{{Lyrics |ዘማሪ=ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ |Artist=Eyerusalem Negiya |ሌላ ፡ ሥም=ጄሪ |Nickname=Jerry |ርዕስ=የዜማ ፡ ጊዜ |Title=Yeziema Gizie |አልበም=ቀን ፡ ሳለ |Album=Qen Sale |Volume=2 |ዓ.ም.=፳ ፻ ፬ |Year=2012 |Track=1 |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic |Lyrics=<poem>


ዘሩን ፡ ከእምባው ፡ ጋር ፡ የዘራ ምርኮ፡ ተወስዶ ፡ የፈራ ማሲንቆን ፡ አፍሮ ፡ የደበቀ ጠላቱ ፡ ወድቆ ፡ ደቀቀ

ቡቃያ ፡ ደርሶ ፡ አፈራ ወይኑ ፡ ዘለላው ፡ ጐመራ በደስታ ፡ ነዶውን ፡ አጨደ ማሲንቆውን ፡ አወረደ

አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ

የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ይኽው ደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ዳርቻዬን ፡ አሰፋልኝ ፡ ካስማዬንም ፡ አጸናልኝ ይሄው ፡ ቆመዋል ፡ አግሮቼ ምርኩዝ ፡ ሆኖልኝ ፡ አባቴ ተሰብሯል ፡ የሃፍረት ፡ ቀንበሬ ፡ ሞልቶታል ፡ አፌን ፡ ዝማሬ ሞገስ ፡ በረከት ፡ ከደጄ ፡

ገብቷል ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
አዝ

የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡

ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ

አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ

በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ
በምሥጋና(፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና
በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና

ልቤ ፡ በሃሴት ፡ በደስታ ፈሰሰ ፡ ቀኔ ፡ ዕልልታ ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ ወጥቼ ድምጼን ፡ ላሰማ ፡ ለአምላኬ

ጭጋጉ ፡ ይሄው ፡ ገፈፈ ሀዘን ፡ ትካዜው ፡ አለፈ ላሞግሰው ፡ እንደገና በድል፡ ዝማሬ ፡ ምሥጋና

የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ

ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ

ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x)

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ

አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ

በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ በምሥጋና(፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና በምሥጋና(፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ በምሥጋንና(፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና poem