From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ፀሐይ ፡ አሽቆልቁላ ፡ በምዕራብ ፡ ስትጠልቅ
ለምሽት ፡ ተረኛ ፡ ለጨረቃ ፡ ስትለቅ
ጐኔን ፡ ላሳርፈው ፡ ከቀኑ ፡ ድካሜ
ስተኛ ፡ እንቅልፌ ፡ ሲያደርሰኝ ፡ በህልሜ
ህልሜ ፡ ቅዥእት ፡ ሆኖ ፡ ጨለማው ፡ በርትቶ
እጥፍ ፡ ሲሆን ፡ ሌቱ ፡ ሲረዝም ፡ ምሽቱ
አቤቱ ፡ ወደአንተ ፡ ድምጼን ፡ አሰማለሁ
ፈጥነህ ፡ እንደትመጣ ፡ እለምንሃለሁ
አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ
የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ
ፀጥ ፡ ረጭ ፡ ባለው ፡ ሰዓት
ኮቴ ፡ በሌለበት ፡ ሁሉ ፡ ቤቱ ፡ ከቶት ፡ እፎይ ፡ በሚልበት
ሃሳቤን ፡ ሚጋራ ፡ ጆሮ ፡ የሚሰጠኝ
ሲጠፋ ፡ ከጐኔ ፡ ጭንቄን ፡ ሚካፈለኝ
የሕይወቴ ፡ ብርሃን ፡ በጽልመት ፡ ሲሞላ
የልቤ ፡ ትርታ ፡ በሃይል ፡ ሲመታ
አቤቱ ፡ ወደአንተ ፡ ድምጼን ፡ አሰማለሁ
ፈጥነህ ፡ እንድትመጣ ፡ እለምንሃለሁ
አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ
የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ
ድንጋይ ፡ ተንተርሶ ፡ ያንቀላፋው ፡ ያዕቆብ
መልካም ፡ ራዕይ ፡ አይቶ ፡ ተስፋው ፡ ሲያብብ
የቀድሞው ፡ ታሪኩን ፡ ሥሙን ፡ ለውጠኀው
የብዙዎች ፡ አባት ፡ እስራኤል ፡ ነህ ፡ አልከው
ጭኑ ፡ የተነካ ፡ እግሩ ፡ የሚያነክስ
ሁለት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ ነግቶለት ፡ ሲመለስ
ልታድነኝ ፡ ብትወድ ፡ ፈጥነህ ፡ ጐህ ፡ ሳይቀድ
ሊነጋ ፡ አያቅላላ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሳትመጣ
አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ (ከጐኔ)
የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ (፪x)
አትራቅ
|