ዋጋ ፡ ስጠው (Waga Setew) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Eyerusalem Negiya 2.jpg


(2)

ቀን ፡ ሳለ
(Qen Sale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሊጠፋ
ድንገት ፡ ሊሰበር ፡ እንደሸክላ
ላጭሩ ፡ ዘመኔ ፡ ቀጠልኩለት ፡ ዕድሜ
መላ ፡ ዘይጃለሁ ፡ እፎይ ፡ ትበል ፡ ነፍሴ

አዝ፦ ለሕይወቴ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ማግኘቴ
ከሞት ፡ ወዲያ ፡ እሻገር ፡ ዘንድ ፡ ላልሞት ፡ ሕያው ፡ ሆኜ
ሰረገላው ፡ አሳፈረኝ ፡ ሊያሻግረኝ ፡ ማዶ
ጠርቶኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እረፍቱ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ወዶ (፪x)

ሞት ፡ እንደው ፡ አይቀርም ፡ ሰው ፡ ግን ፡ ሞት ፡ ይፈራል
ከበሩ ፡ ላይ ፡ ደርሶ ፡ ሊወስደው ፡ ሲመጣ ፡ በእምባ ፡ ዐይኑ ፡ አይቶታል
ነፍሱን ፡ ይወስዳታል ፡ ድምጹን ፡ ሳያሰማ
ላይመልሰው ፡ ዳግም ፡ አንዴም ፡ ሳያቅማማ
ነፍሱን ፡ ይወስዳታል ፡ ኮቴ ፡ ሳያሰማ
ላይመልሰው ፡ ዳግም ፡ አንዴም ፡ ሳያቅማማ

በድኑን ፡ ታቅፈው ፡ ወዳጅ ፡ ዘመዶቹ
ቢያለቅሱ ፡ አይመለስ ፡ ደረት ፡ እየደቁ
በእርግጥ ፡ በኢየሱስ ፡ አምኖ ፡ ካልዳነ ፡ ሰው
ዋይ ፡ ዋይ ፡ ይበሉለት ፡ ደግመው ፡ ያልቅሱለት
ግን ፡ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ አምኖ ፡ ከዳነ ፡ ሰው
እልል ፡ ይበሉለት ፡ ለቅሷቸውን ፡ ትተው

አዝ፦ ለሕይወቴ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ማግኘቴ
ከሞት ፡ ወዲያ ፡ እሻገር ፡ ዘንድ ፡ ላልሞት ፡ ሕያው ፡ ሆኜ
ሰረገላው ፡ አሳፈረኝ ፡ ሊያሻግረኝ ፡ ማዶ
ጠርቶኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እረፍቱ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ወዶ (፪x)

ከንቱ ፡ ለሆነ ፡ ነገር ፡ ታይቶ ፡ ለሚጠፋ
ለሕይወት ፡ ዋስትና ፡ አጥተህ ፡ ወንድሜ ፡ አትልፋ
ክርስቶስን ፡ አምነህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ ፡ ለሕይወትህ
ታይቶ ፡ የሚጠፋ ፡ እንዳያታልልህ
ነይ ፡ እህቴ ፡ ና ፡ ወንድሜ
ዘመኑ ፡ አልቋል ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ አትበል
የመዳን ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ እንዳትወላውል
ከጨለማ ፡ ከሞት ፡ ከሞት ፡ አምልጥ ፡ እሩጥ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ለሕይወትህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ

የመዳንህ ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ እባክህ ፡ ወገኔ
አትወላውል ፡ አትባክን ፡ ትረፍ ፡ ከኩነኔ (፪x)

ትረፍ ፡ ከኩነኔ (፪x)