From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የእግዚአብሔርን ፡ መኖር ፡ ሠማዩ ፡ ነገረኝ ፡ ምድሩ ፡ አወራኝ
ቀኑ ፡ ምሽት ፡ ሲሆን ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ ፡ አረጋገጠልኝ
ያለ ፡ የነበረ ፡ ደግሞም ፡ የሚኖረው ፡ ዘለዓለም ፡ በክብሩ
ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ስለህልውናው ፡ ይመሰክራሉ (፪x)
ለሚመረመር ፡ ለባዕድ ፡ አእምሮ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነገር
በከንቱ ፡ መድከም ፡ መሆን ፡ ተላላ ፡ እጅግ ፡ መሞኘት
ሳይዩ ፡ የሚያምኑ ፡ ብጹአን ፡ ሆኑ
ለስሙ ፡ አምነው ፡ በቤቱ ፡ ጸኑ
መዳን ፡ አገኙ ፡ ከሞት ፡ ተረፉ
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ይልቅ ፡ ብዙ ፡ አተረፉ
ለእኛ ፡ ለደካሞች ፡ ይሄ ፡ እውነት ፡ በራ ፡ ለእኛ ፡ ለምስኪኖች
ለእኛ ፡ ለደካሞች ፡ ይሄ ፡ እውነት ፡ ታየ ፡ ለእኛ ፡ ለምስኪኖች
አዝ፦ የእግዚአብሔርን ፡ መኖር ፡ ሠማዩ ፡ ነገረኝ ፡ ምድሩ ፡ አወራኝ
ቀኑ ፡ ምሽት ፡ ሲሆን ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ ፡ አረጋገጠልኝ
ያለ ፡ የነበረ ፡ ደግሞም ፡ የሚኖረው ፡ ዘለዓለም ፡ በክብሩ
ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ስለህልውናው ፡ ይመሰክራሉ (፪x)
ያወቀ ፡ ሊመስል ፡ ጠቢብ ፡ የሆነ ፡ እጅግ ፡ የላቀ
ሰነፍ ፡ መሆኑን ፡ ከሰው ፡ ሊደብቅ ፡ ልቡ ፡ እያወቀ
ምኞቱን ፡ ሊያደርግ ፡ አምላኩን ፡ ክዶ
ከህሊና ፡ ሙግት ፡ ሊያመልጥ ፡ ፈልጐ
ድፍረት ፡ ቢሞላው ፡ በውስጡ ፡ ክፉ
ከንቱ ፡ ሃሳቡን ፡ አወራ ፡ አፉ
ሞኞችና ፡ ድሆች ፡ እግዚአብሔር (፪x) ፡ ኧረ ፡ እንደው ፡ ይላሉ
ብሎ ፡ ደመደመ ፡ ተስፋ ፡ ቢሶች ፡ ናቸው ፡ ጥበብን ፡ ስላጡ (፪x)
ነፍሱ ፡ ጌታን ፡ ብትፈልገው ፡ እራሱን ፡ አምላክ ፡ አደረገው
የእግዚአብሔር ፡ ፍጥረታት ፡ . (1) .
በድፍረት ፡ ነው ፡ . (2) . ፡ ክህደቱ
የወንዙ ፡ የተራራው ፡ የባሕር ፡ የውቅያኖስ
ፈጣሪውን ፡ ያሳያል ፡ የፍጥረት ፡ ግርማ ፡ ሞገስ
አለ ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ
አለ ፡ ይላሉ ፡ እግዚአብሔር
አለ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኦሆ
አለ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
|