From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ቀድሞ ፡ ወፉ ፡ ሳይጮህ ፡ ጠዋት ፡ በማለዳ
ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ መጣ ፡ ልጆቹን ፡ ሊያነቃ
ማን ፡ ይላከኝ ፡ ብሎ ፡ ስራውን ፡ ሊሰራ
በጠዋት ፡ ለወደደው ፡ ተሰጠው ፡ አደራ
ዓለም ፡ ቀውጢ ፡ ሆና ፡ እጅግ ፡ ተጨንቃለች
በል ፡ ስጣት ፡ መድሃኒት ፡ ፈውስ ፡ አታተማለች
ፍጠን ፡ ልጄ ፡ አለው ፡ ሳይመሽብህ ፡ ቀኑ
መርቆ ፡ ሰደደው ፡ እንዲቀና ፡ መንገዱ
ቢነቃም ፡ ማለዳ ፡ እጅ ፡ እግሬን ፡ እያለ
ከቤቱ ፡ የወጣው ፡ አርፍዶ ፡ ነበረ
ከመንገዱ ፡ ሳለ ፡ ገና ፡ ሳያጋምስ
ጠለቀበት ፡ ጀምበር ፡ ከቦታው ፡ ሳይደርስ
መራመድ ፡ ቢጀምር ፡ ብርሃኑ ፡ ጨላልሞ
ተሰብሮ ፡ ወደቀ ፡ መልዕክቱን ፡ አንግቦ
ምን ፡ ይጠቅመው ፡ ታዲያ ፡ በጸጸት ፡ መንደዱ
መሮጡ ፡ በበጀው ፡ ብሩህ ፡ ሳለ ፡ ቀኑ
አዝ፦ ቀን ፡ ሳለ ፡ ልሩጥ ፡ ሳይጨልም ፡ ብርሃኑ
ሳይመጣ ፡ ጽልመቱ ፡ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ
(ልሩጥ) ወገግ ፡ ሲል ፡ ቀኑ
(ልሩጥ) ሳይጠልቅ ፡ ጀምበሩ
(ልሩጥ) ሳይደክም ፡ ጉልበቴ
(ልሩጥ) ሳይዝል ፡ ሰውነቴ
ሳይደክም (ልሩጥ) ፡ ጉልበቴ
ሳይዝል ፡ ሰውነቴ
ሳይመጣ (ልሩጥ) ፡ ጽልመቱ
ሳይዘኝ ፡ ድባቡ
ትንፋሽ ፡ ያለው ፡ ፍጥረት ፡ መሽቶለት ፡ ሲነጋ
አለው ፡ ብዙ ፡ ተግባር ፡ ዛሬን ፡ እንዲተጋ
አለው ፡ ብዙ ፡ ልፋት ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ጥረት
ነገም ፡ ሌላ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ደግሞ ፡ ሂደት
ሳይተጉበት ፡ ዛሬ ፡ ሳይኖሩ ፡ ለዛሬ
አንዳች ፡ ሳይጨበጥ ፡ ሲገፋ ፡ ያ ፡ ዕድሜ
ምን ፡ ሊፈይድ ፡ ታዲያ ፡ በጸጸት ፡ መንደዱ
መሮጡ ፡ ይበጃል ፡ ምቹ ፡ ሳለ ፡ ቀኑ
አዝ፦ ቀን ፡ ሳለ ፡ ልሩጥ ፡ ሳይጨልም ፡ ብርሃኑ
ሳይመጣ ፡ ጽልመቱ ፡ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ
(ልሩጥ) ወገግ ፡ ሲል ፡ ቀኑ
(ልሩጥ) ሳይጠልቅ ፡ ጀምበሩ
(ልሩጥ) ሳይደክም ፡ ጉልበቴ
(ልሩጥ) ሳይዝል ፡ ሰውነቴ
ሳይደክም (ልሩጥ) ፡ ጉልበቴ
ሳይዝል ፡ ሰውነቴ
ሳይመጣ (ልሩጥ) ፡ ጽልመቱ
ሳይዘኝ ፡ ድባቡ
"እራሱን ፡ የሚወቅስ ፡ እራሱንም ፡ ሚዘልፍ
ስንቱ ፡ ነው ፡ በቤቱ ፡ እለት ፡ በእለት ፡ ሲያልፍ
ዛሬ ፡ የትላንት ፡ ውጤት ፡ መሆኑ ፡ ሚገባው
አንዳንዱ ፡ ዘግይቶ ፡ በረፋዱ ፡ ላይ ፡ ነው
እንግዲያው ፡ በቀረው ፡ በተረፈው ፡ ዘመን
ኋለእኛው ፡ ይበርታ ፡ ይበቀል ፡ ትናንትን
የወደቀ ፡ ይነሳ ፡ ይሆን ፡ አዲስ
ሃይልን ፡ በሚሰጠው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ"
|