ነፍሴ ፡ አጥታልህ (Nefsie Atetaleh) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Eyerusalem Negiya 2.jpg


(2)

ቀን ፡ ሳለ
(Qen Sale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ
እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ
ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ
(፪x)

ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ከነካው ፡ ከለወጠው
ሰንብቷል ፡ ያኔ ፡ ለጋ ፡ ሳለሁ
ከውስጠቴ ፡ ዘልቆ ፡ ገብቶ
ቤቱ ፡ አስቀረኝ ፡ ነፍሴን ፡ ማርኮ
(፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ
እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ
ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ
(፪x)

ፀጋህና ፡ ምህረትህ ፡ ለመዳኔ
ምክንያት ፡ ሆነኝ ፡ ለማምለጥ ፡ ከኩነኔ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ በሰራኀው
ታላቅ ፡ ስራ ፡ እኖራለሁ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ በሰራኀው
ታላቅ ፡ /ገድል ፡ ይሄው ፡ አለሁ

አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ
እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x)
ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ
ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ
(፪x)

ወደእግዚአብሔር ፡ የሚያደርሰው
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የሰው ፡ ልጅ ፡ በከንቱ ፡ እንዳይለፋ
ሁሉን ፡ ፈጸመ ፡ ሰጠው ፡ ተስፋ

የዳነ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ በማንነቱ
ከቶ ፡ አይደለም ፡ መወደዱ ፡ መመረጡ
ዓለም ፡ ገና ፡ ሳይፈጠር ፡ በክርስቶስ
የመረጠውን ፡ አጸደቀው ፡ አከበረው
ማንም ፡ እንዳይመካ ፡ በስራው ፡ አይደለም
ማንም ፡ እንዳይታበይ ፡ በስራው ፡ አይደለም
(፪x)