ከአፌ ፡ አላወርድም (Keafie Alawerdem) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Eyerusalem Negiya 2.jpg


(2)

ቀን ፡ ሳለ
(Qen Sale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

 
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥስምክን
አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x)

ውኃ በማጣት ፡ እንደደረቀ ፡ መሬት
አግኝታ ፡ እስክትረካ ፡ ነፍሴ ፡ እያት ፡ ስትዋትት
ሃይልና ፡ ሞገስህ ፡ በሞላው ፡ መቅደስህ
ፍቀድልኝና ፡ ልየው ፡ ያን ፡ ፊትህን

እንጨትና ፡ ውኃ ፡ በሌለበት ፡ ቦታ
እኔ ፡ ግን ፡ እሄዳለሁ ፡ ውድዬን ፡ ፍለጋ
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ መድህኔ
ጠግቤ ፡ እኖራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ ሬድኤቴ
ፍቅርህ ፡ መድሃኒት ፡ ነው ፡ ፈውስ ፡ ለሕይወቴ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥምክን
አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x)

የተመኘሁትን ፡ ያሰብኩትን ፡ ይዤ
ግን ፡ አልረካሁኝም ፡ አለሁኝ ፡ ተክዤ
ጐተራዬ ፡ አልሞላም ፡ ፍላጐቴ ፡ አልቆመ
የውስጠቴን ፡ ርሃብ ፡ ይሄ ፡ አላተገበም

ወደ ፡ አንተ ፡ እጠራለሁ ፡ ሙጥኝ ፡ እልሃለሁ
ያገኘሁህ ፡ እለታ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ሰው ፡ መልካም ፡ ምግብ ፡ በልቶ ፡ እንዲጠግብ
ነፍሴ ፡ ትጠግባለኝ ፡ በክብርህ ፡ በግርማህ
ሰው ፡ መልካም ፡ ምግብ ፡ በልቶ ፡ እንዲጠግብ
ነፍሴ ፡ ትጠግባለኝ ፡ ጌታዋን ፡ ስታስብ

ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ፍሰሃ
ኢየሱስ ፡ ብኖር ፡ በበረሃ
ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ብርሃን
ኢየሱስ ፡ ባልፍም ፡ በጨለማ
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ ሬድኤቴ
ፍቅርህ ፡ መድሃኒት ፡ ነው ፡ ፈውስ ፡ ለሕይወቴ
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ መድህኔ
ጠግቤ ፡ እኖራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ

በመጠበቂያዬ ፡ በማማዬ ፡ ሆኜ
እጠብቅሃለሁ ፡ እንዳይህ ፡ አምኜ
ዝለቴ ፡ ድካሜ ፡ ይወገድ ፡ አፍረቴ
በሰፈሬ ፡ እንድታልፍ ፡ እንድትገባ ፡ ቤቴ

ባላሰብኩት ፡ ሰዓት ፡ ባልጠበኩት ፡ ቦታ
በጊዜ ፡ ሰሌዳ ፡ በአንተ ፡ አቆጣጠር
የጠበኩህ ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ትመጣለህ
ረሃቤን ፡ ጥማቴን ፡ ያኔ ፡ ታረካለህ
የጠበኩህ ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ትመጣለህ
ረሃቤን ፡ ጥማቴን ፡ አንተው ፡ ታረካለህ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥምክን
አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x)