From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ
እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያስብ ፡ ኖሮ
ኃጢአቴን ፡ ልናዘዝ ፡ ህሊናዬ ፡ ሲወቅሰኝ
ምህረትም ፡ ልማጠነው ፡ ደጅ፡ ባስጠናኝ
ውድቀቴ ፡ ሳይገደው ፡ ባላገጠ ፡ ፊቱ ፡ በጠቆረ
ፍቅሩ ፡ ቀዝቅዞብኝ ፡ ድምጹ ፡ በሻከረ
እንኳንስ ፡ ልጁ ፡ ሊያረገኝ
ሥሙን ፡ ለመጥራት ፡ ባስከፈለኝ (፪x)
እንኳንስ ፡ ቤቱ ፡ ለመኖር
ከደጁ ፡ መጣል ፡ በተሳነኝ
ከደጁ ፡ መጣል ፡ በናፈቀኝ
አዝ፦ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም
ከቶ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም
ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ወሰን ፡ ቁጥር ፡ የለው
ከወዳጅም ፡ ወዳጅ ፡ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ
የወደቀን ፡ አይቶ ፡ እንዳላየ ፡ አይሸሽ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም (፬x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያይ ፡ ኖሮ
እንደ ፡ ሰው ፡ ቢያስብ ፡ ኖሮ
ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ሳጣ ፡ ሲጐድል ፡ ሙሉ ፡ ቤቴ
ከንፈር ፡ ቢመጥልኝ ፡ ርቆ ፡ ከአጠገቤ
ባሕሪው ፡ ተለውጦ ፡ ቀስ ፡ እአለ ፡ በሽሽ ፡ በራቀ
ወዳጅነት ፡ ቀርቶ ፡ አዛኝ ፡ በመሰለ
ነፍሴን ፡ ሲከፋት ፡ ዝም ፡ ስል
ሃዘኔ ፡ ንቀት ፡ ቢመስል (፪x)
ውስጤ ፡ ማቅ ፡ ለብሶ ፡ ከሰው ፡ ቢያርቅ
እንደኮራሁ ፡ ቢያስበኝ ፡ እንደተኩራራሁ ፡ ቢያስበኝ
አዝ፦ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም
ከቶ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ አይደለም
ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ወሰን ፡ ቁጥር ፡ የለው
ከወዳጅም ፡ ወዳጅ ፡ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ
የወደቀን ፡ አይቶ ፡ እንዳላየ ፡ አይሸሽ
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም (፬x)
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩ ፡ አያረጅም
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ አይለዋወጥም
|