እምነት (Emnet) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Eyerusalem Negiya 2.jpg


(2)

ቀን ፡ ሳለ
(Qen Sale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

"ብዙ ፡ እንቆቅልሽ ፡ እሄሄ
ዛሬም ፡ ከብዶባቸው
ዘወትር ፡ በልማድ ፡ ከበራፉ ፡ ደርሰው
ይመጣሉ ፡ ይገባሉ ፡ ተቀምጠው ፡ ይወጣሉ
ያመነ ፡ ሰው ፡ ሲድን ፡ ያዩ
ምታስበኝ ፡ መች ፡ ነው ፡ ይላሉ
ጌታ ፡ እንደሚችል ፡ አፋቸው ፡ ቢያወራ
ልባቸው ፡ ቢፈተሽ ፡ አሄሄ
ጥቂት ፡ እምነት ፡ የለም
በጥርጣሬ ፡ እምነታቸው ፡ ጐሎ
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ጌታ ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
ከነጥያቄያቸው ፡ ተመልሰው ፡ ሄዱ
ትላንት ፡ የሚደክሙ ፡ አሃሄሄ
"

ለአመታት ፡ በሃፍረት ፡ ከሰው ፡ ያገለላት
ወዳጅ ፡ አልባ ፡ ሆና ፡ ብቻዋን ፡ ያስቀራት
ለህመሟ ፡ መድሃኒት ፡ መፍትሄ ፡ ሲጠፋ
በልቧ ፡ ስትጠብቅ ፡ ኢየሱስን ፡ በተስፋ
ቀሚሱን ፡ በእምነት ፡ ብትነካ ፡ በእጆቿ
እንደ ፡ እምነቷ ፡ ሆነ ፡ አዬ ፡ . (1) .
የበሽታው ፡ ምንጭ ፡ ከስሩ ፡ ደረቀ
በሰውነቷ ፡ ላይ ፡ . (2) .

አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ፡ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ፡ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ፡ ያድናል

እምነት ፡ በመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ
እግዚአብሔርን ፡ ማወቅ ፡ ይበልጣል ፡ ከሁሉ
ኤልሻዳይ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆነውን ፡ ጌታ
እንዳይችል ፡ አሰብነው ፡ ሆነን ፡ በልብታ
እግዚአብሔር ፡ እራሱ ፡ እንዲሆን ፡ ቢነግረን
ማመን ፡ ይሳነናንል ፡ ከቃሉ ፡ ርቀን

አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ፡ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ፡ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ፡ ያድናል

ባሪያዬ ፡ በጠና ፡ ታሞ ፡ ከቤቱ ፡ ላይ
በቃልህ ፡ እዘዝ ፡ ብቻ ፡ ካልጋ ፡ ላይ ፡ ይነሳል
ከጣሪያዬ ፡ በታች ፡ ልትገባ ፡ አይገባህም
ተናገረኝ ፡ እንጂ ፡ ይህ ፡ ቀን ፡ አያልፈኝ
ጌታም ፡ ተደነቀ ፡ በዚህ ፡ ሰው ፡ እምነት
ብላቴናው ፡ ድኗል ፡ ሂድ ፡ ወደቤትህ
አለው ፡ ኤልሻዳዩ ፡ ሁሉን ፡ የሚቻለው
ቃሉን ፡ ሰደደና ፡ ባሪያውን ፡ ፈወሰው

አዝ፦ (ለሚያምን) ኧረ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(ለሚያምን) ቀሚሱ ፡ ያድናል
(ለሚያምን) ቃሉ ፡ ይፈውሳል
(ለሚያምን) ኢየሱስ ፡ ያድናል

እምነት ፡ በመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ
እግዚአብሔርን ፡ ማወቅ ፡ ይበልጣል ፡ ከሁሉ
ኤልሻዳይ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆነውን ፡ ጌታ
እንዳይችል ፡ አሰብነው ፡ ሆነን ፡ በልብታ
እግዚአብሔር ፡ እራሱ ፡ እንዲሆን ፡ ቢነግረን
ማመን ፡ ይሳነናንል ፡ ከቃሉ ፡ ርቀን

አዝ፦ (ለሚያምን) ጨለማው ፡ ይበራል
(ለሚያምን) ብበሩ ፡ ይከፈታል
(ለሚያምን) ተራራው ፡ ይናዳል
(ለሚያምን) በእምነታችን ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ ይለዋል