From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ምሥጋና ፡ ልሰዋ ፡ በተዋበ ፡ ዜማ
ሁሉ ፡ በሚቀለው ፡ ሊዘምር ፡ ከእኔ ፡ ጋር
ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ተነሳሁ ፡ ልመታ ፡ ከበሮ
አምላኬ ፡ አርቆታል ፡ የልቤን ፡ እሮሮ
አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ፡ ያለው ፡ ይዘምር
(ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ፡ ቀንበር
(ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ፡ ምሥጋና
(ኦሆኦሆሆ) ለጌታ ፡ እንደገና
ላከበረኝ ፡ ጌታ ፡ በምወደው ፡ ዜማ
በሚገባኝ ፡ ቋንቋ ፡ ቅኔን ፡ በሙገሳ
ምቱልኝ ፡ ከበሮ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ
በማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ ላክብረው ፡ በሆታ
የባርያዪቱን ፡ ውርደት ፡ አምላኳ ፡ አየና
ስድብ ፡ ነቀፋዋን ፡ አስቦ ፡ እንደገና
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ቀንን ፡ ሲቆጥርላት
መገፋቷን ፡ አይቶ ፡ ዛሬ ፡ ደረሰላት
ቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ብሏል ፡ አፌም ፡ ይዘምራል
ጓዳዬ ፡ በቅኔ ፡ በዝማሬ ፡ ደምቋል
አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ፡ ያለው ፡ ይዘምር
(ኦሆኦሆሆ) ተሰብሮለት ፡ ቀንበር
(ኦሆኦሆሆ) ይሰዋ ፡ ምሥጋና
(ኦሆኦሆሆ) ለጌታ ፡ እንደገና
ላከበረኝ ፡ ጌታ ፡ በምወደው ፡ ዜማ
በሚገባኝ ፡ ቋንቋ ፡ ቅኔን ፡ በሙገሳ
ምቱልኝ ፡ ከበሮ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ
በማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ ላክብረው ፡ በሆታ
የእንባ ፡ ስቅታዬ ፡ መርዶ ፡ በወጣበት
ዛሬ ፡ ግን ፡ ከቤቴ ፡ ምሥጋናን ፡ ሞላበት
አምላኬ ፡ በክብሩ ፡ ወደ ፡ እልፍኜ ፡ ገብቷል
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ከሩቁ ፡ ይጠራል
ወዳጅ ፡ ዘመዶቼ ፡ ጌታ ፡ ይሰራልኝን
አይተው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አከበሩት ፡ ውዴን
አዝ፦ (ኦሆኦሆሆ) ደስ ፡ ያለው ፡ ይዘምር
(ኦሆኦሆሆ) ሆኖ ፡ ከእኒ ፡ እጋራ
(ኦሆኦሆሆ) የተደረገለት
(ኦሆኦሆሆ) እስቲ ፡ ማን ፡ አለና
ላከበረኝ ፡ ጌታ ፡ በምወደው ፡ ዜማ
በሚገባኝ ፡ ቋንቋ ፡ ቅኔን ፡ በሙገሳ
ምቱልኝ ፡ ከበሮ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ
በማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ ላክብረው ፡ በሆታ
ልስገድ ፡ በሽብሸባ ፡ ይጨመር ፡ ጭብጨባ
ይህ ፡ አይበቃምና ፡ መቅደስ ፡ ውስጥ ፡ ስገባ
ምቱልኝ ፡ ከበሮ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ
በማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ ላክብረው ፡ በሆታ (፪x)
|