Eyerusalem Negiya/Qen Sale/Awqalehu
|ዘማሪ=ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
|Artist=Eyerusalem Negiya
|ርዕስ=አውቃለሁ
|Title=Awqalehu
|አልበም=ቀን ፡ ሳለ
|Album=Qen Sale
|Volume=2
|ዓ.ም.=፳ ፻ ፬
|Year=2012
|Track=7
|ቋንቋ=አማርኛ
|Language=Amharic
|Lyrics=
ግራና ፡ ቀኜን ፡ ከፊት ፡ ከኋላ
ሲጨልምብኝ ፡ ባጣ ፡ ማረፊያ
ተስፋዬ ፡ ያልኩት ፡ በእጄ ፡ ይዤ
ድንገት ፡ ሲከዳኝ ፡ ብቀር ፡ ተክዤ
የተውከኝ ፡ ሲመስለኝ ፡ አምላኬ ፡ ከላይ
ምድር ፡ ጐርብጣ ፡ ቢዘጋ ፡ ሰማይ
አሃሃ ፡ አውቃለሁ
አንተ ፡ ሁልጊዜ ፡ ትክክል ፡ እንደሆንክ
አውቃለሁ ፡ ተናግረህ ፡ ማትፈጽም ፡ ቀላባይ ፡ እንዳልሆንክ
አዝ፦ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ሃሳብ ፡ እንዳለህ
ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ
ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ (፪x)
ሀጥያቴ ፡ ሲጋለጥ ፡ ለአሉታ ፡ ወሬ
በነበር ፡ ሆኖ ፡ ሳይቀር ፡ ነገሬ
የሽንፈት ፡ ቃላት ፡ ከአፌ ፡ እንዲወጣ
ሲወተውተኝ ፡ ምክንያት ፡ ቢያጣ
ሙሾ ፡ ሲደረድር ፡ ይኸው ፡ ጠፋሁ ፡ ብዬ
በገናዬን ፡ ስጥል ፡ ሊስቅ ፡ ባላንጣዬ
አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ዞርበል ፡ አንተ ፡ ክፉ ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ አያለሁ
አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው ፡ አመሰግናለሁ
አዝ፦ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ሃሳብ ፡ እንዳለህ
ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ
ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ
ፍቅር ፡ ነህ
በእኔ ፡ ላይ ፡ አላማህ ፡ ልዩ ፡ ነው
ልዩ ፡ ነው
}}