From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በኃይለኛው ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ኃይለኛ
በሚዳኘው ፡ ላይ ፡ ሲሰየም ፡ ዳኛ
በዓለቃው ፡ ላይ ፡ አለ ፡ አለቃ
የሰው ፡ ሹመቱ ፡ ልኩ ፡ ሲያበቃ
ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
የከበረ ፡ የታወቀ ፡ የገነነ ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ ሥመኛ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዝነኛ
የለህ ፡ አቻ ፡ እኩያ ፡ የለህ ፡ ምትክ ፡ አምሳያ
አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉም ፡ መሪ
ከላይ ፡ የመጣው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ካለልክ ፡ ከፍ ፡ ያደረገው
እኛ ፡ ዝቅ ፡ ልንል ፡ እርሱ ፡ ግን ፡ ሊልቅ ፡ ነው
የተገባው ፡ ነዉ ፡ ከሁሉ ፡ ሊበልጥ (፪x)
ኧረ ፡ ይህንን ፡ ጌታ
ሊሽር ፡ ማንስ ፡ ሊረታ
ሹመቱ ፡ ዙፋኑ ፡ ጽኑ
ገደብ ፡ የለው ፡ ስልጣኑ
አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ
በሃይለኛው ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ሃይለእኛ
በሚዳኘው ፡ ላይ ፡ ሲሰየም ፡ ዳኛ
በዓለቃው ፡ ላይ ፡ አለ ፡ አለቃ
የሰው ፡ ሹመቱ ፡ ልኩ ፡ ሲያበቃ
ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ
የከበረ ፡ የታወቀ ፡ የገነነ ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ
ከስም ፡ ሁሉ ፡ ስመኛ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዝነኛ
የለህ ፡ አቻ ፡ እኩያ ፡ የለህ ፡ ምትክ ፡ አምሳያ
አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ
በማስተዋል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለ
እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ የከበረ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ክምድር ፡ በታችም ፡ የገነነ
ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ይመሰክራል ፡ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ይንበረከካል
ለእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ለኢየሱስ ፡ አለቅነት ፡ ተገብቶታል
አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ
የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ
|