ይችላል (Yichelal) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

እናንተ ደካሞች ብዙ ሸክም የከበዳችሁ
ወደኔ ቅረቡ ከቀንበራችሁ ላሳርፋችሁ
ብሏልና ጌታ ሸክሜን ሁሉ አንድም ሳላስቀር
አራግፋለሁ ጭንቀቴን ሁሉ ከእግሩ ስር
እኔን ያጎበጠኝ በርሱ ፊት ምንድነው
አልፈታም ሚለው ችግሬ የትኛው ነው
ጥያቄዬን ሁሉ እሰድዳለሁ ወደላይ
ለእርሱ አስረክቤ እኔ እላለሁ እፎይ

ይችላል ( #4 )
ይችላል ሽባውን መተርተር
ይችላል ዲዳውን ማናገር
ይችላል ተራራውን መናድ
ይችላል ደመናውን ማውረድ

አለቀልኝ ብዬ ያከተመው ነገሬን ይዤ
ስለምን ልቀመጥ አንተ እያለህ በሀዘን ተክዤ
ትናንትን ስትሰራ ስታደርግ በአይኔ አይቼ
ስለምን ልጠርጥር ዛሬ የተራራውን ትልቀት ፈርቼ
ተራራው ለኔ እንጂ ባንተ ፊት ምንድነው
የሚገዳደርህ ሀይል የትኛው ነው
አንዳች ነገር የለም ካንተ አቅም በላይ
ሁሉን የምትችል ጌታ አይደለህም ወይ

ይችላል ( #4 )
ይችላል እንቆቅልሽ መፍታት
ይችላል ያዘነን ማፅናናት
ይችላል የወደቀን ማንሳት
ይችላል ጨለማውን ማብራት

ከበበኝ በላይ ያንተ ትልቅነት
ይታየኛል ያንተ ትልቅነት ይከብድብኛል
አምንሀለሁ ጌታ ሁሉ ይቻልሀል
ምን ተስኖህ ሁሉ ይቻልሀል ምን ያቅትሀል?

ከበደኝ በላይ ያንተ ትልቅነት
ይታየኛል ያንተ ትልቅነት ይገዝፍብኛል
አምንሀለሁ አባ ሁሉ ይቻልሀል
ምን ተስኖህ ሁሉ ይቻልሀል ምን ያቅትሀል?

ትሰራለህ ታደርጋለህ የሚሳንህ የለም
ትተክላለህ ትነቅላለህ ከልካይ የለብህም
ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ
ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ


ትሰራለህ ታደርጋለህ የሚሳንህ የለም
ትተክላለህ ትነቅላለህ ከልካይ የለብህም
ክንደ ብርቱ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ
ኤልሻዳይ አምላክ ነህ ሁሉን ትችላለህ

ትችላለህ የጠፋን መመለስ
ትችላለህ በሽታን መፈወስ
ትችላለህ ሸለቆን መሙላት
ትችላለህ የሞተን ማስነሳት