የእሩቅ ፡ አላሚ (Yeruk alami) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

የሩቅ አላሚ ነኝ ግን የቅርብ አዳሪ
የሩቅ አሳቢ ነኝ ግን የቅርብ ተጓዥ ነዋሪ ሰፋሪ

የፈቃድን ሚስጥር እሻና በብርቱ
ግን ልቤ ሊኖረው አወይ ማመንታቱ
በውስጥ ማንነቴ በራለሁ ከሰማይ
ስጋዬ ጎትቶ ያወርደኛል ከላይ

ፍቅርህ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ይነካና
አይኔ እንባ ያፈሳል ትናፍቀኝና
ነፍሴ ተነቃቅታ አንተኑን ስታስብ
መንፈሴ ወዲያውኑ ይጋልባል ሽቅብ

መንፈሳዊነቴ ያኔ ሲበረታ
ሀሌሉያ እያልኩ ከምድር ስፋታ
ያልማል ይመኛል ሰማዩን ምናቤ
ከደመናው በላይ ይሄዳል ሀሳቤ

ያን ግዜ እንዳልደክም ምዬ ተገዝቼ
ፈለግህን ልከተል ለራስ ቃል ገብቼ
በአለም ማዕበል ሲመታ ግለቴ
መች ይታወቀኛል ሲደክም ህይወቴ።

በኑሮ ገጠመኝ ከፍና ዝቅ ስል
በወጣሁበት ልክ እየኝ ሳሽቆለቁል
በረታሁኝ እያልኩ ዝዬ እገኛለሁ
በሁለቱ ክበብ ላይ እሽከረከራለሁ

ከዚህ ሟች ስጋዬ የሚለየኝ ማነው?
ጥማቴም ረሀቤም አንተን ለመምሰል ነው
እንደማትጥለኝ በእርግጥ አውቃለሁ
ግን አንዳንዴ ራሴ ማመን እፈራለሁ።

ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው?
ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ
ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው
ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ

ቢዝል ቢደክም ስጋዬ ዳግም ሊበረታ
በድካሜ ምትራራ ደጉ የኔ ጌታ
እጄን በእጅህ እንደያዝክ እስከ መጨረሻው
እያገዝከኝ በፀጋህ ዘልቄ እሄዳለሁ

ፀጋህ እየረዳኝ እያገዝከኝ
ባንተ ሁሉን እችላለሁ እችላለሁኝ