የፀጋውን ፡ ቁርበት (Ye'tsegawn qurbet) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

የፍጥረት በኩር መጀመሪያ
ፍፃሜ የሆነ መደምደምያ
የሚታይ የማይታየው ዓለማቱ
በእርሱ ተፈትሮዋል ነው ምክንያቱ

የአዳምን እርቃን ሸፈነ ያን ሀፍረት
ህይወት አለበሰው የፀጋውን ቁርበት
የእባቡን እራስ ቀጥቅጦ የቀጣ
በሴቲቱ ዘር ግንድ በስጋ የመጣ

ከጥፋቱ ውሀ መርከብ የሚጠብቅ
የማምለጫው መንገድ እንዲድን ፃድቅ
በይስሀቅ ምትክ የታረደው በግ
በበሩ መቃን ላይ የተረጨው ደም

ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች፪
አየሱስ እየሱስ አለች

ነውር የሌለበት ንፁህ መስዋት
ጣፋጩ ሽታ በእግዚአብሔር ፊት
የመስዋቱ በግ ሊቀ ካህኑ
ስለኛ የሚታይ በመቅደሱ

ከሰማይ ሰማያት የወረደው መና
የፀናው አለት ያፈለቀው ውሀ
የመውጫው መስላል ከምድር ወደ ስማይ
የማህዘን እራስ ክቡር ህያው ድንጋይ

የሁሉ ፊተኛ ጅማሬ ፍፃሜ
የህይወት ምህራፍ ከፋች ደግሞም ድምዳሜ
የፍጥረት እስትንፋስ ህልውና መሪ
ፊተኛ ቀዳሚ የአለም ፈጣሪ

ኢየሱስ ጥንትም የነበር
ኢየሱስ ዛሬም ደግሞ ያለ
ኢየሱስ ዘላለም የሚኖር
ኢየሱስ ሁሌ እንደክበረ

ከላይ ከአርያም ከክብር ዙፋኑ
ከተንቆጠቆጠው ካማረው መንበሩ
ወርዶ በኛ መሀል ድንኳኑን ተከለ
ቃል ስጋ በመሆን በእኛ አደረ

ከሀጢያት በስተቀር በሁሉ ያለፈ
ሲኦልን ድል ነስቶ ሞትን ያሸነፈ
መንግስቱ በምድር ሁሉ ሊጠቀልል
ሊነግስ ዘላለም ተመልሶ ይመጣል

ያለ የነበረ አልፋና ኦሜጋ
አንዳች ፍትረት የለም ክብሩን የሚጥጋ
ከስሞች የሚበልጥ ስምም ተስትቶታል
ያልልክ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አድርጎታል

ኢየሱስ ጥንትም የነበር
ኢየሱስ ዛሬም ደግሞ ያለ
ኢየሱስ ዘላለም የሚኖር
ኢየሱስ ሁሌ እንደክበረ

ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች
በዐይኑዋ ማዳኑን አየች
ነፍሴ በፍቅሩ ገመድ ታስረች
አየሱስ እየሱስ አለች

መስቀልህ በልቤ እንዲሳል ደምቆ
ማንነህ እንዲታይ በእኔ ልቆ
ይህ ጥማት በውስጤ ስርፆ ገባ
እፋልግሀለውነጋ ጠባ