የበረሃው ፡ ጞዴ (Ye'berehaw guade) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ማን ነበረ ከጎኔ ያኔ?
 ያልተለየኝ ከአጠገቤ?
ሀዘን ሲያቆስለው ልቤን
ሳስታውሰው መከራዬን
የተወለድኩበትን ቀን
 ስረግመው ደጋግሜ።

አንዱ ሳያበቃ
የኑሮዬ ሲቃ
ሲደራረብብኝ ውስጤን ሲደቁሰው
እውነት ነበረኝ ወይ? እውነተኛ አፅናኝ
የውስጥ ጥልቅ ስሜቴን አውቆ የተረዳኝ

ፈራጅ እንጂ አፅናኝ ነበረኝ ወይ?
የመሰለውን የተሰማውን ባይ
አዝነው ሲያስተክዙኝ
መልሰው ሲያቆስሉኝ
ብሶቴን ቀስቅሰው አልቃሻ አረጉኝ

የበረሀው ጓዴ የጥሻው ዘመዴ
ለካስ ወዳጅ አለኝ ባያዩህ ይህ አይኔ
ከወንድም አብልጦ በጣም የሚጠጋ
ተረድቶ የሚረዳ ስለኔ ያለው ዋጋ።

አለሁ ባዬ መከታዬ ኢየሱስ ጌታዬ
ልጄ አትፍሪ ተደገፊ ትከሻዬ ሰፊ
እያለ ያፅናናኝ ያበረታኝ ክንዴ
ከጎኔ የቆመ ያባባለኝ ውዴ
እንባዬን ጠራርጎ አፌን በሳቅ ሞላ
መከራዬ ሄደ ቀረ ወደ ዃላ።

ኢየሱስ(*2) እውነተኛ ወዳጅ
ኢየሱስ(*2) ከልብ የሚወዳጅ
ኢየሱስ(*2) ታማኝ ባልንጀራ
ኢየሱስ(*2) ቀን ሲጥል የማይከዳ
ኢየሱስ(*2)
ኢየሱስ(*2) ቀን ሲጥል የማይከዳ