ያቺ ፡ ጉጠት (Yachi gutet) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ሳበኝ ወዳንተ እሮጣለሁ መልካሙ እረኛ
ድምፅህን እየሰማሁ እከተልሀለሁ
ሳበኝ ወዳንተ እሮጣለሁ መልካሙ እረኛ
ኮቴህን እየሰማሁ እከተልሀለሁ

ያቺ ጉጠት ኢሳያስን የዳሰሰች
አንደበቱን ንግግሩን የለወጠች
ዛሬም ትምጣ በነፍሰ ስጋ በመንፈሴ
እንዲወገድ ከህይወቴ ድንዛዜ

ሀይል ያስፈልገኛል የእግዚአብሔር እሳት
ሙሴ በቁጥቋጦ ውስጥ ስትነድድ ያያት
ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በህይወቴ
አንድ ጊዜ ንካኝ ይለወጥ ህይወቴ

ከአለም መጎምዠት ከስጋዊ መሻት
ውስጡ ወና ባዶ ውሸትና ቅዠት
ከምናቡ አለም በአምሮት ከመስከር
ህልሜ መና ሆኖ በምኞት እንዳይቀር

ነጥቆ በሚያወጣው ከዘቀጠው ሀሳብ
በመንፈስህ ላምልጥ ከሌለበት እረብ
ክብርህ ናፍቆኛል እንዲገለጥ በህይወቴ
አንድ ጊዜ ንካኝ ይለወጥ ህይወቴ

የመንፈስህ እሳት የክብርህ ሙላት
ሲያገኘኝ ሲነካኝ ያንተ መገኘት
እንደ ሌላ ሰው እለወጣለሁ
ደጋግመህ ንካኝ መቼ እረካለሁ
እንደ ሌላ ሰው እለወጣለሁ
ደጋግመህ ንካኝ መቼ እረካለሁ

ህልውናህ መንፈስህ ነፍሴን ደስ ያሰኛል
ህልውናህ መገኘትህ ነፍሴን ያረካታል
የናፈቀኝ የተጠማሁት የምፈልገው የሚናፍቀኝ
ክብርህን ነው ክብርህን መንፈስህን ነው ክብርህ
ክብርህን ነው ክብርህን መንፈስህን ነው መንፈስህ