ወለል ፡ ያለ (Welel yale) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 7:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ
ከርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ
ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ
ከርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ

ጠአመ ቢስ ልሳኔ አንደበቴም ገራ
ህይወቴ ጨፍጋጋ እንዳይሆን መራራ
አመዴን አራግፎ ወዛም ያደረገኝ
በሰዎች ሁሉ ፊት በሞገስ አቆመኝ

ደብዛዛው መልኬ ደመቀ በስሙ
ጭንጋፉ ገፄ ተዋበ በደሙ
በድቅድቁ ለሊት በማይሸፈን ፊት
እንዳብለጨልጭ ጌታዬን ልክ እንደ መስታወት

የፊቱ ብርሀን ፍንትው ያለ ጮራ
እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ
የፊቱ ብርሀን ወለል ያለ ጮራ
እየጨመረ መጣ በላዬ ላይ በራ

በራ(#2) የህይወቴ ጭጋግ ወገግ አለ በራ ፈካ
በራ(#2) የህይወቴ ጭጋግ ወገግ አለ በራ

በቀን ከሚበረው አስደንጋጭ ፍላፃ
ነፍሴ እርፍ አለች በአንተ ወጥታ ነፃ
የቀትሩ ጋኔን እንዳያስፈራራኝ
መቅሰፍት ወደ ቤቴ እንዳይገባ ጋረደኝ

መላዕክቱን ስለኔ እያዘዛቸው
እንዳልሰናከል ያዙኝ በእጆቻቸው
ተኩላ እና እባቡን እረጋግጬ
ድል አድራጊ ሆንኩ በኢየሱስ ወጥመዱን አምልጬ

በባላንጣዬ ፊት ራሴን ቀብቶታል
ያስፈራኝ ጠላቴ በተራው ፈርቶኛል
በባላንጣዬ ፊት ራሴን ቀብቶታል
ያስፈራኝ ጠላቴ በተራው ፈርቶኛል

ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ኦሆሆ
ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና

ማረፊያዬ ነው የቀትር ጥላዬ
ከርሱ የተነሳ ፈርቶኛል ጠላቴ
ማረፊያዬ ነው የቀትር ጥላዬ
ከርሱ የተነሳ ፈርቶኛል ጠላቴ

ምን ይዋጠኝ ብዬ ለነገ እንዳልሰጋ
ፅኑ የተስፋ ቃል እኔ አለኝ እሱጋ
በእጄ የያዝኩት ቢወድቅ ቢናድ የካብኩትም
ኢየሱስ ስላለኝ አልርበተበትም
በትርህ ምርኩዜ ለሽምግልናዬ
ቀሪ ሀብቴ ነው ቢጎብጥ ጀርባዬ
እስከ ሽበቴ ይሸከመኛል
የማታ የማታ መጦሪያዬ ኢየሱስ ሆኖኛል

ቸርነት ምህረቱ ሁሌ ይከተሉኛል
ዘልአለም በቤቱ አዝልቆ ያኖረኛል
ቸርነት ምህረቱ ሁሌ ይከተሉኛል
ዘልአለም በቤቱ አዝልቆ ያኖረኛል

ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና ኦሆሆ
ፀና (*2) የህይወቴ ካስማ አለቱ ላይ ፀና

ቱሩፋቴ ነው የማታ እንጀራዬ
ከርሱ የተነሳ ያምራል እርጅናዬ
ቱሩፋቴ ነው የማታ እንጀራዬ
ከርሱ የተነሳ ያምራል እርጅናዬ