ወዶኛልና (Wedognalna) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ምን ውጦኝ ነበር አንተን ባላገኝ
ባትቀበለኝ ልጅ ባታረገኝ አሄሄ
ሰጥተኸኝ ጥበብ ክህሎት ችሎታ
አምላኬን ትቼ ለሰው ሆይ ሆይታ አሄሄ
ነበር እጣዬ አይኔ ባይበራ
የሲዖል ማገዶ ኑሮ ከሞት ጋር
በራልኝና የህይወት መንገድ
ኑሮ ጀመርኩኝ ባንተ ስወደድ

ዛሬ ግን ለኢየሱስ እዘምራለሁ እዘምራለሁ
ዘምሬ የማልጠግበው ስለርሱ ነው
ዛሬ ግን ለክብሩ አወራለሁ አወራለሁ
አውርቼ የማልጠግበው ስለርሱ ነው

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ከህይወት ምንጭ ውሀ ፈልቆ ጠጣሁና
ጥሜ ቆረጠልኝ ዳግም ላልጠማ
የክብሩ ነፀብራቅ በላዬ ላይ በርቶ
ከክብር ወደ ክብር አሻገረኝ መርቶ

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

የፊቱ ብርሀን አበራ በህይወቴ
ጉሙ በነነ ፈካ ህይወቴ
ተጥለቀለኩኝ በደስታ በሀሴት
ከላይ ወረደልኝ ፍፁም በረከት

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው
አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ
ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው
አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ

ከዘልአለም ማዕድ ከእንጀራው በልቼ
ላልራብ ረካሁ ኢየሱስን አግኝቼ
የመቅበዝበዝ ህይወት ከእንግዲህ አበቃ
አይኖቼን ከፈተ ሙት መንፈሴ ነቃ

ወዶኛልና አዳናት ነፍሴን
አረ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን
ወዶኛልና ድናለች ነፍሴ
እስቲ ማን ልበለው ይሄን ኢየሱሴን

ማን ልበለው ውዴን ምን ልበለው
አንጀቴን የሚያርስ ማብራሪያ ባገኘሁ
ማን ልበለው ውዴን ደስ እንዲለው
አንጀቴን የሚያርስ ዜማ ቃል ባገኘሁ