ስለ ፡ ማን? (Sele man) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ቆይ ከአንተ ውጪ ስለማን ስለምን? ስለነማን? ላውራ?
አንደበቴን ስከፍት ስምህ ይቀናኛል
ፍቅርህ በልቤ ላይ እንደ አምድ ተተክሏል
ኢየሱስ(*2) ኢየሱስ ኢየሱስ እያልሽ ዘምሪ ያሰኘኛል።

መፅሐፉ ተከፍቶ እስኪዘጋ ድረስ
ስላንተ ያወራል ድንቁ ጌታ ኢየሱስ
ነቢያት ሀዋርያት የመሰከሩልህ
መንፈስቅዱስ መጥቷል አንተኑ ሊገልጥህ
አብ አባትህ ብሏል 'የምወደው ልጄ'
አንተን አንተን ብልስ ነው ታድያ ወድጄ?

ሲነጋና ቀኑ ሲመሽ
ከእስትንፋስህ ከፊትህ እንዳልሸሽ
ፍቅርህ በዝቶ እኔን መውደድህ
አሸነፈኝ ከማን ላወደዳድርህ።

ኦሆሆሆ በቃ አልችልም ኦሆሆሆ ካንተ ልለይ
ኦሆሆሆ ደስ አይለኝም ኦሆሆሆ ፊትህን ሳላይ

( Choir )
ህይወት ሆኖልኛል የመአዛ ሽታ
አረ ማን ሊተካህ ሆኖ ባንተ ቦታ
ኑሮዬ ባንተ ላይ የተደገፈ ነው
ከእቅፍህ ቢያወጡኝ አቅሜ ምንድነው?
የአፍህ ቃል እኮ ነው የማዳንህ ስራ
ምህረትህን ያሳየኝ በራሴ እንዳልኮራ
እንዳንተ የሚሆን ስላጣሁ ፈልጌ
ሌላውን አልሰብክም እኔ አንተን ሸሽጌ።

በጋ ክረምት ፀደይ በልጉ
በሀዘን ደስታ በክፉ በደጉ
በማለዳ በረፋዱ
ያዋጣኛል ስምህን መውደዱ።
ኦሆሆሆ በየቀኑ ኦሆሆሆ በየወሩ
ኦሆሆሆ ከአመት አመት ኦሆሆሆ አንተን ማለት
ኦሆሆሆ እኔ አልችልም ኦሆሆሆ ካንተ ልለይ
ኦሆሆሆ ደስ አይለኝም ፊትህን ሳላይ

ህይወት ሆኖልኛል የመአዛ ሽታ
አረ ማን ሊተካህ ሆኖ በአንተ ቦታ?