From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ (Eyerusalem Negiya)
|
|
፫ (3)
|
አልበም (3)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2021
|
ቁጥር (Track):
|
፯ (7)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:17
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች (Albums by Eyerusalem Negiya)
|
|
ወጥመዱን ዘርግቶ ነፍሳትን ሲጠልፍ
የሰውን ልጅ በሙሉ በሀጥያት ሲነድፍ
ሲፎክር ሲዘብት ማን አለብኝ ብሎ
ዲያብሎስ ወደቀ ዛሬ ድል ተነስቶ
ወደ ሲዖል ወርዶ መንጋጋው ፈልቅቆ
ነፍሳትን አዳነ ኢየሱስ ተናጥቆ
የሞት ፍርሀት ቀንበር ቆሌው ተገፈፈ
በቃ አለቀለት ሰይጣን ተሸነፈ
ሞት ሆይ የታለ ማሰሪያህ
ሲዖል ሆይ የታለ መውጊያህ
ሞት ሆይ የታል ጩኸትህ
ሲዖል ሆይ የታለ ቀስትህ
ይሄ ሁሉ ክብር ይሄ ሁሉ ዝና(*2) ኦኦ ዝና
ተገብቶሀልና ጌታ አንተ ነህ ገናና ገና ኦኦ ገና
ሞትን ድል የነሳ
የይሁድ አንበሳ
ሞትን ያሸነፈው
ክብር የተረፈው
እንግዲህ የአዳም ዘር ትንሳኤ ሆነለት
በኢየሱስ መሞት ሞት ተሸነፈለት
ምድር እልል ትበል ጌታዋ ተነስቷል
በትንሳኤው ጉልበት መዳን መጥቶላታል
በመከራው ብዛት በጭንቅ በፍዳው
ለኔ ለአንቺ ለአንተ ነው እንዲህ የተጎዳው
በእርሱ ያመነ ማንም እንዳይጠፋ
አንድያ ልጁ ነው የእግዚአብሔር ስጦታ
ሞት ሆይ የታል ማሰሪያህ
ሲዖል ሆይ የታለ መውጊያህ
ሞት ሆይ የታል ጩኸትህ
ሲዖል ሆይ የታለ ቀስትህ
ጩኸት ማስፈራራት ዋይታና ሁካታ ኦኦ ሁካታ
ሞትን ድል በነሳ በጌቶቹ ጌታ ጌታ ኦኦ ጌታ
ፀጥ አለ ድንፋታው
ሽለላው ፉከራው
ስልጣኑን ገፈፈው
ሞትን ያሸነፈው
|