ምትኬ (Mitike) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ቀረብኩ ከችሎት ከፍርድ አደባባይ
ሊገለጥ ሊነገር ታሪኬ እንዲታይ
ብዙ ነው በደሌ ዶሴ ሲወሳ
በነፃ እንድለቀቅ ያሻል የደም ካሳ
በድንገት አንድ ድምፅ ተሰማ ከሰማይ
አገኘው አለሁ ባይ ስለኔ ተወካይ
የስራዬ ዋጋ ነበር የሞት ቅጣት
ምትኬ ሆነልኝ በኔ ፈንታ ሊሞት።

፩-በበደል በሀጥያቴ ሙታን የነበርኩኝ
ለዚህ አለም ገዢ የተንበረከኩኝ
የስጋን ምኞቴን ሁሌ የምሰማ
የቁጣ ልጅ ነበርኩ ምኖር በጨለማ
ነገር ግን እግዚአብሔር ምህረቱ የበዛ
አንድ ልጁን ሰጠኝ እንዲሆነኝ ቤዛ
ክርስቶስን ሳምን ስለው ቤዛ አዳኜ
ተወለድኩ በዚ አለት አዲስ ፍጥረት ሆኜ።

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም
ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ
በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ(2)

፪የወደድኳት አለም ያሞካሸዋት
መልሳ ላትበጀኝ ስትነዳኝ ወደ ሞት
እያሳሳቀችኝ አለሁኝ እያለች
ነፍሴን ልታጠፋ በብርቱ ቸኮለች
ሞት እንደሰነቀች ሳይገባኝ ሚስጥሯ
ቀርቤ ሳለሁኝ ለክፉ ወጥመዷ
የአዳኙ ጥሪ ተሰማኝ ከሩቁ
የምህረት እጆቹ ነፍሴን ተናጠቁ።

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ

አይወዳደርም የሰጠኸኝ ፍቅር
በዚህ አለም ክብር
አይነፃፀርም የሰጠኸኝ ህይወት
በዚ አለም ውበት
አይወዳደርም የሰጠኸኝ ፀጋ
በዚህ አለም ዋጋ
አይነፃፀርም የሰጠኸኝ ደስታ
በዚህ አለም ሁካታ
በቃ ተለውጫለሁ ልቤን ሰጥቼሀለሁ
ግባ የክብሬ ንጉስ አንተ ሁን የቤቴ ራስ(#2)

፫ እርግማኔን ሁሉ በመስቀል ቸንክሮ
በነፃ ለቀቀኝ ወጥመዴን ሰባብሮ
የሞት ፍርሀት ጫና ከኔ ላይ ወደቀ
ጠላቴ ላይከሰኝ ነፍሴን አፀደቀ።
እኔ የእኔ አይደለሁም ሞቻለሁ ለራሴ
በቀራንዮ መስቀል በሞቱ አብሬ
በተሻለው ኪዳን በትንሳኤው ጉልበት
ኑሮ ጀምሬያለሁ ሆኜ አዲስ ፍጥረት።

ትቼ የመጣሁትን አለም
ላልመለስበት በምንም ቆርጫለሁ ልከተልህ ኢየሱሴ በላዬ ልሾምህ ላደርግህ ንጉሴ(#2)