From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ (Eyerusalem Negiya)
|
|
፫ (3)
|
አልበም (3)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2021
|
ቁጥር (Track):
|
፩ (1)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:56
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች (Albums by Eyerusalem Negiya)
|
|
ጭው ባለው በበረሀ
ምንም በሌለበት ውሀ
ባዶ ሆኖ ምንጩ ደርቆ
በእጄ የያዝኩት ሁሉ አልቆ
አይኔን ባቀና ወደ ላይ
ስመለከት ወደ ሰማይ
በተስፋ ተሞላ ልቤ
ያየኝን ሳይ አሻቅቤ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
ቃልኪዳኑን የማይረሳ
የወደቀን የሚያነሳ
አለን በሰማይ ሊቀካህን
በድካማችን የሚራራልን
እንዳየ እንደሰማ የማይፈርድ
ሀብታም ደሀን እኩል የሚወድ
ፊት አይቶ ፍርድ የማያደላ
ለጨነቀው የሚሆን ከለላ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
ጉድለቴን ሳየው ባዶነቴን
ይሰብከኛል አወይ ውድቀቴን
እዬዬ እላለሁ እጮሀለሁ
የሚረዳው አምላክ እንደሌለው
ሰማይና ምድርን የፈጠረ ጌታ
አይኔ ተከፍቶ ሳይ አለ በዚ ቦታ
ሰማይና ምድርን የፈጠረ ጌታ
አይኔ ተከፍቶ ሳይ አለ በዚ ቦታ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
ለካ ያየኛል ኢየሱስ ለካ
ይመለከተኛል ለካ
አይቶ ሰምቶ የሚራራ
አለ ከእኔ ጋራ
አቤቱ በስምህ ታመንኩ ለዘላለም
ጥላዬ ነህና ከእንግዲ አልፈራም
ከማህፀን ጀምሮ የያዙኝ እጆችህ
እግሮቼን አፀኑ እነዚያ ክንዶችህ
ከአመፀኛው ጡጫ
ከአስፈሪ እርግጫ
ነፍሴን አስጥለሀል ከሚውጠኝ ጉድጓድ
ዘመኔን እያየኸው ስለምን ልጨነቅ
አንተን እየጠራሁ አመልጣለሁ ከጭንቅ
|