እረግረጉ ፡ ደረቀ (Eregregu dereke) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

እግዚአብሔር ከኔ ጋር ባይሆንማ ኖሮ
የጠላቴ ቁጣ በኔ ላይ በርትቶ
በህይወት ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበረ
ታሪኬን ሊያስቀረው እያለ እንዳልነበረ

ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም
እንዳሰበው ክፉ አላገኘኝም
ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም
እንዳሰበው ጠላት አላጠፋኝም

ጠላቴማ ሊለያየኝ ስንት ጊዜ ሞከረ
ሊነጥለኝ ከእውነት ስንት ጊዜ ጣረ
ጌታ ጣልቃ እየገባ ምክሩን እያፈረሰ
የሸፈተው ልቤን ወደራሱ መለሰ

በፀሎቴ አለፍኩት አልልም ያንን ሁሉ ወጀብ
በጉልበቴስ መች በተንኩት አስፈሪውን አጀብ
በፅናቴ ተወጣሁት አልልም ያን ዳገት አቀበት
በብልጠቴስ መች ሾለኩኝ ከዛ ሁሉ ውድቀት

ፀጋህ ተትረፍርፎ ምህረትህ በዝቶልኝ
የማልችለው ተቻለኝ ከባዱ ቀለለኝ
እረግረጉ ደረቀ ጎርባጣውም ቀና
የዘመመው ማገሬ እንደገና ፀና

ሰባራውን ድልድይ እየገጠመ ጎርፉን እየገደበ
ስፍገመገም እጄን በእጁ ይዞ እግሬን አሻገረ
በስሙ አለት ላይ አፀናኝና እንዳወራ የሱን ዝና
ዜማን እና ቅኔን አስታጠቀኝ ዘምርለታለሁ ገና
አዜምለታለሁ ገና
እቀኝለታለሁ ገና
እኖርለታለሁ ገና
አገለግላለሁ ገና