አወራታለሁ (Aweratalehu) - ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ
(Eyerusalem Negiya)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢየሩሳሌም ፡ ነጊያ ፡ አልበሞች
(Albums by Eyerusalem Negiya)

ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው
የሚወደድ ማይጠገብ ለሚጠራው
ነፍሴን ከሞት መለሰ
ፍቅርህ እንደ ጅረት እየፈሰሰ
መንፈሴን አረሰረሰ ህይወቴን እየፈወሰ
መንፈሴን አረሰረሰ ስጋዬን እየፈወሰ

ለስብራቴ ፍቱን መድሀኒቴ
መድመቂያ ካባዬ ለማንነቴ
ስምህ ነው ትምክህቴ መቆሚያ አለቴ
ማገሩ ለቤቴ ፅኑ መሰረቴ

የክብር ንጉስ ነህ ደጉ ኢየሱስ ለዘልአለም ንገስ
በመንበሬ በኑሮዬ በሰገነቴ በከፍታዬ
ለዘላለም ንገስ አንተ የክብር ንጉስ

ወደዱህ ወደዱህ ያዩህ የቀመሱህ
ባንተ ደስ አላቸው ሀሴት አደረጉ
መአዛህ መልካም ነው ስንቱን ለወጠ
ስንቱን አጣፈጠ
ፍቅርህ ልዩ ነው ስንቱን ለወጠ ስንቱን አጣፈጠ

የእኔነቴ ማዕረግ የክብር መጠሪያዬ
ኢየሱስ አንተው ነህ ጌጤ መዋቢያዬ
ነፍሴ እንድታውቅህ አንተን እሰብካታለሁ
ልቤም እንዲወድህ ሁሌ አስብሀለሁ

አወራታለሁ ለነፍሴ ስላንተ አብዝቼ ሁልጊዜ
እነግረዋለሁ ለልቤ ፍቅርህ እንዲበረታ በሀሳቤ
አወራታለሁ ለነፍሴ ስላንተ አብዝቼ ሁልጊዜ
እነግረዋለሁ ለልቤ ፍቅርህ እንዲበረታ በሀሳቤ