ዛሬ ግን በቤትህ (Zare Gen Be Beteh) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 8:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ያልጠፋሁት በምህረትህ ነው X 2
ያልጠፋሁት ፀጋህ በዝቶ ነው
ያልጠፋሁት በምህረትህ ነው

ዛሬ ግን በቤትህ አቁመኸኛል X 2
ላንተ ይሁን ምስጋና X 3

በሰዎች ፊት ስታይ ደህና እመስላለሁ
ነበር መቅበዝበዝ ግን ሕይወቴን የሞላው
ጠማማው መንገዴን ዞር ብዬ ሳየው
እጅግ ያሳዝናል ምንኛ መራር ነው

ዛሬ ግን በቤትህ አቁመኸኛል X 2
ላንተ ይሁን ምስጋና X 3

አንተን ባለማውቅ ከቤትህ እርቄ
ዘመናት አስቆጠርኩ ስማቅቅ ወድቄ
ያሳለፍኩት ሕይወት ምንኛ ይመራል
ዛሬ ግን አዳኜ ሕይወተቴን ለውጧል

ዛሬ ግን በቤትህ አቁመኸኛል X 2
ላንተ ይሁን ምስጋና X 3

እንደ በደሌ መጠን አልተከፈለኝም
ችግሬንም አይተህ ዝም ብለህ አላለፍክም
እሩህሩህ አምላክ ነህ እጅግም ይቅር ባይ
ነፍሴን አድነሃል ከዘላለም ስቃይ

ዛሬ ግን በቤትህ አቁመኸኛል X 2
ላንተ ይሁን ምስጋና X 3

ልጄ ሆይ ተመለስ ማርኩህ ብለኸኛል
ዳግምም ለክብርህ ጌታ አቁመኸኛል
አልፋና ዐሜጋ ይድረስህ ምስጋና
ለኔ ያደረከው እጅግ ድንቅ ነውና

ዛሬ ግን በቤትህ አቁመኸኛል X 2
ላንተ ይሁን ምስጋና X 3