ታደገን (Tadegen) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ታደገን እግዚአብሔር ታደገን
ታደገን እየሱስ ታደገን
ከጨለማ ስልጣን በእርሱ ነጻ ወጣን

ባራቱም ማእዘን ወጀብም ቢነሳ
ምድር ብትናወጥ ሰማይም ቢናጋ
ከሰማያት በላይ ስሙ የገነነው
የይሁዳ አንበሳ የእኛም ጌታ እኮ ነው

ታደገን እግዚአብሔር ታደገን
ታደገን እየሱስ ታደገን
ከጨለማ ስልጣን በእርሱ ነጻ ወጣን

ልንጠፋ ነው ስንል እኛም ሊያልቅልን
የጌቶቹ ጌታ እየሱስ አለልን
መሸሸጊያ እርሱ ነው የጸና ግንባችን
ስሙ በሁሉ ላይ ገኗል አምላካችን

ታደገን እግዚአብሔር ታደገን
ታደገን እየሱስ ታደገን
ከጨለማ ስልጣን በእርሱ ነጻ ወጣን

የገነነው ስሙ የሱስ ስለሆነ
አጋንንት በሽታ መቼ ሊቆም ቻለ
ከሱ የተነሳ ቀንበር ተሰበረ
እኛም ነፃ ወጣን እየሱስ ከበረ

ታደገን እግዚአብሔር ታደገን
ታደገን እየሱስ ታደገን
ከጨለማ ስልጣን በእርሱ ነጻ ወጣን

እንደ ጠላት ሀሳብ ቢሆንማ ኖሮ
በጠፋን ነበረ ገና ድሮ ድሮ
የጌታ ግን ሀሳብ መልካም ስለሆነ
በምስጋና ቆምን ጠላትም አፈረ

ታደገን እግዚአብሔር ታደገን
ታደገን እየሱስ ታደገን
ከጨለማ ስልጣን በእርሱ ነጻ ወጣን

ለገነነው ስሙ እጅግ ለከበረው
አልፋና ዖሜጋ ምስጋና ይድረሰው
ለዘላለም አለም ስሙ ይግነንልን
እየሱስ ጌታችን እሱ ይክበርልን