ኦ ታላቅ ደስታ ነው (O Talake Deseta Neew) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ኦ ታላቅ ደስታ ኦ ታላቅ ክብር X 2
ሲገለፅ ከሰማይ ሲመጣ ልናየው
የነገስታት ንጉስ ባባቱ ቀኝ ያለው
ኦ ታላቅ ደስታ ነው

እየሱስ ከሙታን ፈንቅሎ ሲነሳ
የሞትና ሲኦል ትጥቃቸው ተፈታ
ታላቅ ደስታ ሆነ በመቃብር ቦታ
አረ ማን ይዞታል የጌቶቹን ጌታ

ኦ ታላቅ ደስታ ኦ ታላቅ ክብር X 2
ሲገለፅ ከሰማይ ሲመጣ ልናየው
የነገስታት ንጉስ ባባቱ ቀኝ ያለው
ኦ ታላቅ ደስታ ነው

በክብር ይመለሳል አምሮና ተውቦ
ከመላክቱ ጋራ በክብር ታጅቦ
አስተውል ወንድሜ ተዘጋጅተህ ጠብቅ
እየሱስ ሲመጣ አብሮ ለመነጠቅ

ኦ ታላቅ ደስታ ኦ ታላቅ ክብር X 2
ሲገለፅ ከሰማይ ሲመጣ ልናየው
የነገስታት ንጉስ ባባቱ ቀኝ ያለው
ኦ ታላቅ ደስታ ነው

እየሱስ ይመጣል ዘንዶውም ይጣላል
በጨለማው መንግስት ታላቅ ረበረሻ ይሆናል
በፃድቃን ከተማ እየሱስ ያበራል
የርሱ የሆኑትን ሁሉ ይሰበስባል

ኦ ታላቅ ደስታ ኦ ታላቅ ክብር X 2
ሲገለፅ ከሰማይ ሲመጣ ልናየው
የነገስታት ንጉስ ባባቱ ቀኝ ያለው
ኦ ታላቅ ደስታ ነው

ያን ጊዜ የወጉት በክብር ያዩታል
ወድቀውም በምድር ለርሱ ይሰግዱለታል
ምድር አትችለው የይሁዳ አንበሳ ነው
ፀሃይም ብርሃኑን ከቶ አትቋቋመው

ኦ ታላቅ ደስታ ኦ ታላቅ ክብር X 2
ሲገለፅ ከሰማይ ሲመጣ ልናየው
የነገስታት ንጉስ ባባቱ ቀኝ ያለው
ኦ ታላቅ ደስታ ነው