ልዑል ሆይ ለስምህ (Leul Hooy Le Semeh) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ወደ ማደሪያህ ወደ ዙፋንህ
ወደ ማደሪያህ ወደ መቅደስህ
እንመጣለን የሱስ ልናወድስህ X 2
እንገባለን ጌታ ልናወድስህ

ልዑል ሆይ ለስምህ ክብር ምስጋና ይገባል X 2

ክብርህ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ ብሏል
ምስጋናህም በምድር እጅጉን አይሏል X 2

በምስጋናም አንተ ነህ በክብርም አንተ ነህ
በዘላለም ዙፋንህ ከፍ ብለህ ትኖራለህ X 2

ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ X 2

ልዑል ሆይ ለስምህ ክብር ምስጋና ይገባል X 2

ክብርህ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ ብሏል
ምስጋናህም በምድር እጅጉን አይሏል X 2


የሰራዊት አምላክ እንዳንተ ያለ ማነው
ብርታትና ሐይል እውነት የከበበው
ባህርና የብሱን አንተ ትገዛለህ X 2
የሞገዱን መናወጥ ጸጥ ታደርጋለህ

ልዑል ሆይ ለስምህ ክብር ምስጋና ይገባል X 2

ክብርህ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ ብሏል
ምስጋናህም በምድር እጅጉን አይሏል X 2

ነገስታቶች ሁሉ ላንተ ይገዛሉ
ታላቅ ነው እግዚአብሔር ሃያል ነው እያሉ
እኛም እንሰዋለን ለክብርህ ምስጋና X 2
ስምህ በምድር ላይ ከፍ ብሏልና

ልዑል ሆይ ለስምህ ክብር ምስጋና ይገባል X 2

ክብርህ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ ብሏል
ምስጋናህም በምድር እጅጉን አይሏል X 2

ወደ ማደሪያህ ወደ ዙፋንህ
ወደ ማደሪያህ ወደ መቅደስህ
እንመጣለን የሱስ ልናወድስህ X 2
እንገባለን ጌታ ልናወድስህ