ልቤ ታመነብህ ጌታ (Lebe Tamenebeh Geta) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ልቤ ታመነብህ ጌታ ታማኝ ነህ 4 X

ታማኝ ነህ . . . ታማኝ
ታማኝ ነህ . . . ታማኝ

ልቤ , ይታመንሃል ጌታ 8 X

የተናገርከኝን ምንም ሳልጠረጥር
በምሽት ወጥቼ ከዋክብት ስቆጥር 2 X
አንድ እኔን ብቻዬን ነበር የጠራኸኝ
ቃልህ ተፈፀመ እንዲህ አበዛኸኝ
የተናገርከውን ያልከውን ፈፅመሃል
ጌታዬ ታማኝ ነህ ልቤ ይታመንሃል 2 X

ልቤ , ይታመንሃል ጌታ 8 X

ገና ሳልሰራ ስጋ አጥንት ሳይኖረኝ
አንተ ነህ እግዚአብሔር አስቀድምህ ያወከኝ 2 X
ባንተ የተፈጠሩ ቀኖቼ በሙሉ
በእጅህ ይዘሃቸዋል በመዝገብህ አሉ
ስለዚህ እጥላለሁ ሕይወቴን ባንተ እጅ
እኔ ለእኔ አላውቅም ፈጣሪዬ አንተ እንጂ 2 X

ልቤ , ይታመንሃል ጌታ 8 X

ከፊት እየቀደምክ በሳት በደመና አምድ
ሕይወቴን ስትመራ በማላውቀው መንገድ 2 X
ሰልፌን ተሰልፈህ መግበህ ሕይወቴን
እጅህን ከፍተኸልኝ ባርከኸዋል ቤቴን
ነፍሴ ታውቀዋለች ስራህ እጅግ ድንቅ ነው
በሕይወቴ ዘመን ባንተ እታመናለሁ 2 X

ልቤ ታመነብህ ጌታ ታማኝ ነህ 4 X

ታማኝ ነህ . . . ታማኝ
ታማኝ ነህ . . . ታማኝ