ክብር ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ (Keber Lelew Alehu Befitu) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
ዙፋኑንም ፡ ፍቅር ፡ የሞላው
በልጁ ፡ ደም ፡ እኔን ፡ ለገዛው (፪x)
ክብር ፡ ምስጋናዬ ፡ ይድረሰው

አዝ፦ ክበር ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ንገስ ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ግነን ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ (፪x)
ኃያል ፡ ክንደ ፡ ብርቱ

በገናዬን ፡ ላንሳ ፡ ጌታዬን ፡ ላወድስ
ስግደት ፡ ዝማሬዬ ፡ ከማደሪያው ፡ ይድረስ
ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነውና
ክብር ፡ ንገስ ፡ ልበል ፡ በመዝሙር ፡ በልልታ

አዝ፦ ክበር ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ንገስ ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ግነን ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ (፪x)
ኃያል ፡ ክንደ ፡ ብርቱ

በዘላለም ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ
በታላቅ ፡ ምረቱ ፡ በቤቱ ፡ ያቆመኝ
እንዳገለግለው ፡ ለርስቱ ፡ የለየኝ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ልሆን ፡ ስልጣንን ፡ የሰጠኝ

የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
ዙፋኑንም ፡ ፍቅር ፡ የሞላው
በልጁ ፡ ደም ፡ እኔን ፡ ለገዛው (፪x)
ክብር ፡ ምስጋናዬ ፡ ይድረሰው

አዝ፦ ክበር ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ንገስ ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ
ግነን ፡ ልለው ፡ አለሁ ፡ በፊቱ (፪x)
ኃያል ፡ ክንደ ፡ ብርቱ

ሥሙ ፡ ብርታቴ ፡ ሆኖኛል
ስዝል ፡ ደግፎ ፡ አቁሞኛል
በእርሱ ፡ ፀንቼ ፡ ቆሜያለሁ (፪x)
ጠላቴን ፡ እረግጫለሁ