ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለአለም (Ke Zare Jemero Eseke Zelealem) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል X 3 X 2

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
እግዚአብሔር በህዝቡ ዙሪያ ነው X 2 X 2

ጠላት መስሎት ነበር ይዞ የሚያስቀረን
ሲገዳደር መጣ በባህር ሊጥለን
ግን በድል ተሻገርን እርሱ ሰጠመና
የማዕበሉ ጌታ ከኛ ጋር ነውና X 2

ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል X 3 X 2

ተቅበዝብዘና ሳለን በምድረ በዳ ላይ
በማጉረምረም ሆነን ስናይ ወደ ሰማይ
ረሰረስን ከላይ መና ዘነበና
ቃል ኪዳን አክባሪው ከኛ ጋር ነውና X 2

ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል X 3 X 2

ሲያጓራብን ጊዜ የፍልስጤም ጭፍራ
እኛም ፈርተን ሸሸን ከዚያ ሰልፍ ስፍራ
ያስፈራን ጎሊያድ ጣለው ብላቴና
የሰራዊት ጌታ ከኛ ጋር ነውና X 2

ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል X 3 X 2

ሞት ጥላውን ጥሎ ሊወስደን ሲያደባ
ከነ ሐጢያታችን ሲዖል እንድንገባ
ሕይወት አበዛልን እየሱስ መጣና
ኤልሻዳዩ አምላክ ከኛ ጋር ነውና X 2

ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል X 3 X 2

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
እግዚአብሔር በህዝቡ ዙሪያ ነው X 2 X 2