እኔ የማመልከው (Ene Yemamelekew) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

እኔ የማመልከው ኤልሻዳይ አምላክ ነው
መንግስቱ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነው
በሰማይ በምድር ድንቅንም ያደርጋል
ከአንበሶች ጉድጓድ ዛሬም ይታደጋል X 2

ሐምራዊ ግምጃዬን ከእኔ ሊወስደው
የወርቅ ማርዳውንም ከአንገቴ ሊያወልቀው
የሚገዳደረው ከንቱ ሊደክም ነው
እኔን ያከበረ እግዚአብሔር ሐያል ነው
እኔን ያከበረ እግዚአብሔር ታላቅ ነው
 
እኔ የማመልከው ኤልሻዳይ አምላክ ነው
መንግስቱ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነው
በሰማይ በምድር ድንቅንም ያደርጋል
ከአንበሶች ጉድጓድ ዛሬም ይታደጋል X 2

በግዞት ስላለሁ ጠላት ተደስቶ
ተገዳድሮ ወጣ በትእቢት ደንፍቶ
አስቦ ነበረ ሊያስቀርብኝ ቀንቶ
የሾመኝ አምላኬ መሆኑን ዘንግቶ X 2

እኔ የማመልከው ኤልሻዳይ አምላክ ነው
መንግስቱ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነው
በሰማይ በምድር ድንቅንም ያደርጋል
ከአንበሶች ጉድጓድ ዛሬም ይታደጋል X 2.

ተመራምሮ ሊያገኝ በደልና ስህተት
ሊከሰኝ ፈልጎ ሊያስቀርብኝ ሹመት
የታመነ ነበር እኔ የታመንኩበት
የእግዚአብሔር መንፈስ ምን ስህተት አለበት X 2

እኔ የማመልከው ኤልሻዳይ አምላክ ነው
መንግስቱ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነው
በሰማይ በምድር ድንቅንም ያደርጋል
ከአንበሶች ጉድጓድ ዛሬም ይታደጋል X 2

ምታመልከው አምላክ ያድንህ ብለውኝ
በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ እኔን ወረወሩኝ
ሐያሉ እግዚአብሔር መቼ ተቀድሞ ያውቃል
አፋቸውን ዘግቶ ህይወቴን ታድጓል
አፋቸውን ዘግቶ ነፍሴን አድኗታል

እኔ የማመልከው ኤልሻዳይ አምላክ ነው
መንግስቱ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነው
በሰማይ በምድር ድንቅንም ያደርጋል
ከአንበሶች ጉድጓድ ዛሬም ይታደጋል X 2