እግዚአብሔር ሆይ አንተ (Egeziabeher hoye anete) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 7:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

እግዚአብሔር ሆይ አንተ በዙፋንህ ላይ ነህ × 2
አምረህ ከፍ ብለህ ከብረህ ከፍ ብለህ × 2
ጌታ የሱስ አንተ በዙፋንህ ላይ ነህ × 2
አምረህ ከፍ ብለህ ከብረህ ከፍ ብለህ × 2

በውበትህ በግርማህ እግዚአብሔር ሆይ ልዩ ነህ
በሃይልህ በክብርህ እግዚአብሔር ሆይ ታላቅ ነህ

ሃሌ ሉያ × 3 አ ሃ ሃ

እልፍ አእላፍ መላአክት ላንተ ይሰግዳሉ
ዙፋንህ ስር ወድቀው ቅዱስ ነህ እያሉ
ክብርህ በምድር ላይ ሁሉ ስለሞላ
በሰማይ በምድር ስምህ እጅግ ተፈራ

ሃሌ ሉያ × 3 አ ሃ ሃ

ሞትና ሲኦልን ሁሉ ድል ነስተሃል
ጌታ የሱስ አንተ ዙፋን ተገብቶሃል
ከነገድ ከቋንቋ ህዝብህን ዋጅተሃል
ለአባትህ መንግስት ካኽን አርገኸናል

ማዳንና ሀይልም መንግስትም ያንተ ነው
ክብር የተገባው ከቶ ያላንተ ማነው
በረከት እና ክብር ምስጋናና ሃይልም
ላንተ ላምላካችን ይሁን ለዘላለም