እግዚአብሔር ሊያሳርፍህ (Egeziabeher Liyasarefeh) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ 3X
እግዚአብሔር ሊያሳርፍህ ወዶአልና ተቀበለው 2X

እነሆ ጌታ በርህን ያንኳኳል
እንድትከፍትለት ይለምንሀል
ጊዜው እሩቅ አይደለም ቅርብ ነው
ወስን የመዳን ቀን ዛሬ ነው 2X
 
እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ 3X

በአለም ያለው ሁሉ አይጠቅምህምና
የሱስ አንተን ሊያድን ሞቶልሃልና
ወንድሜ ጌታህን እወቀው
ነፍስህን የሚያሳርፍ አምላክ ነው 2X

እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ 3X

ወገኔ እንዳትጠፋ አልሰማ ብለህ
ጌታህን ተቀበል አዳኝ አድርገህ
በሕይወት መዝገብ ላይ ትፃፋለህ
ወደ እርሱ ብትመጣ ታተርፋለህ 2X

እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ 3X

የሐጢያት ደሞዝ ትርፉ ሞት ነውና
የእግዚአብሔር ማዳን በየሱስ ነውና
ትፈልጋለህ ወይ በሕይወት መኖር
በእምነት ተቀበለው እየሱስን

እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ 3X
እግዚአብሔር ሊያሳርፍህ ወዶአልና ተቀበለው 2X