አዎ ሁሉም ያልፋል (Awo Hulum Yalefal) - ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን
(Evangelical Christ Church in Munich Choir)

Evangelical Christ Church in Munich Choir 1.jpg


(1)

በፈቃዴ ፡ ላምልክህ
(Befeqadie Lamlekeh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሙኒክ ፡ ወንጌላዊት ፡ የክርስቶስ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Evangelical Christ Church in Munich Choir)

ስልጣንም ይሻራል
ነገስታት ያልፋሉ
እንደ ልብስ ያረጃሉ
አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

አዎ ክብርም ያልፋል አዎ ዝናም ያልፋል
አዎ ሁሉም ያልፋል አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

በምድር የምናየው ዘላቂ ቢመስለን
አይደለም ነዋሪ ያበቃል ሁሉም ነገር አንድ ቀን

አዎ ምድርም ያልፋል አዎ ፍጥረት ያልፋል
አዎ ሁሉም ያልፋል አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

መከራም ቢይዘን ችግርም ቢከበን
ሁሉም ጊዚያዊ ነው እግዚአብሔር ዘላለም ህያው ነህ

አዎ ስደት ያልፋል አዎ ችግር ያልፋል
አዎ ሁሉም ያልፋል አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

ሳር ይጠወልጋል አበባም ይረግፋል
ግን ያምላካችን ቃል ዘላለም ሳይለወጥ ይኖራል

አዎ ዘመን ያልፋል አዎ ትውልድ ያልፋል
አዎ ሁሉም አልፋል አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

የቅዱሳን ተስፋ በክብር ይገለጣል
ለሁሉም ይታያል እየሱስ ዘላለም ይነግሳል

አዎ ትላንት አልፎአል አዎ ዛሬም ያልፋል
አዎ ነገም ያልፋል አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ

አዎ ይህም ያልፋል አዎ ይህም ያልፋል አዎ ይህም ያልፋል
አንተ ግን ዘላለም ህያው ነህ